DigArticle

ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች እና ፈፃሚዎች በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Posted 320 days ago (ጥር 23, 2023 ) by Teklu Elias     0 Comments

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በፍትህ ሚኒስቴር የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኖህ ታከለ ተቋሙ የ10 እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅዶችን በማዘጋጀት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በስትራቴጂክ እቅዶቹ ውስጥ በርካታ ፕሮጀክቶች የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን ፕጀክቶች ውጤታማ ለማድረግ ይህ ስልጠና አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

አቶ ኖህ ስልጠናው 2ኛ ዙር መሆኑን በማስታወስ መካከለኛ አመራሩና ፈፃሚው በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ እንዲጎለበትና በፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዉ ከዕቅድ ጀምሮ የሚፈለገዉን ዉጤት እስከ ማስመዝገብ ድረስ ያለዉን ሂደት ከፕሮጀክት አስተዳደር መርህ አንጻር መቃኘት እንዲቻል ሥልጠናው ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

 

የሥልጠናውም ዓላማ በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ የመካከለኛ አመራሩንና የፈጻሚውን የእውቀት ክህሎት ማዳበር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ ስልጠናውን የፍትህ ሚኒስቴር እና ፕሪሳይስ (PRESISE) በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል፡፡


No CommentsYou need to login to comment.