Search

የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባር እና ኃላፊነት


ቀደም ሲል የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የበጀት ዝግጅትና ክትትል ስራን በማካተት ሲሰራ የነበረ ቢሆንም በአዲሱ አደረጃጀት የበጀት ዝግጅትና አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ በዕቅድ፣ በጀትና ፕሮጀክት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬቶሬት ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ሆኖ በስሩ አንድ ቡድን በመያዝ የሚከተሉት ተግባራት እና ኃላፊነት ይኖሩታል:-


1. ከመንግሥት ግምጃ ቤትና ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኘውን ገንዘብ ወደ መስሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፣

2. ለተቋሙ የሚመደበውን በጀት በመንግሥት የፋይናንስ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሠራር ሥርዓቶች ላይ በመመስረት አገልግሎቶችን ይሰጣል፣

3. በተዘረጋዉ አሰራር መሰረት ለዘርፎቹና ለቅርንጫፍ /ቤቶች የተመደበዉን ገንዘብ ለይቶ በተከፈተዉ የባንክ አካዉንት ገቢ ያደርጋል፣

4. መረጃዎች የተሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ በሕግ መሰረት ክፍያዎችን ይፈፅማል፣ የሂሣብ ምዝገባ ያደርጋል፣

5. የሂሳብ ሰነዶች በመለየት ይመዘግባል፣ በቅደም ተከተል እንዲደራጅ ያደርጋል፣ በአግባቡ ተጠብቀዉ መያዛቸዉን ይከታተላል፣

6. የሂሳብ አያያዝ እና የክፍያ አፈጻጸም በደንብና መመሪያ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል ይከታተላል

7. ከመንግስት በየጊዜው የሚተላለፉ አዳዲስ የፋይናንስ መመሪያዎች ያስተዋውቃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

8. በስራ ላይ ያሉ ልዩ ልዩ ቅጾችና ፎርማቶችን በትክክል በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል

9. የሠራተኞች የስራ ላይ መገኘትና የለቀቁ ሰራተኞች ሪፖርት ይሰበስባል፣ የለቀቁትን ለይቶ ከደመወዝ ክፍያ ሰነድ (ፔይሮል)እንዲወጡ ያደርጋል፣

10. ያልተወራረዱ ክፍያዎችን ለይቶ ይከታተላል፣ እንዲወራረዱ ያደርጋል፣

11. ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት በተቀመጠው አሰራር መሰረት ገቢ ይሰበስባል፣ በህጉ መሰረት ለመንግስት ገቢ ያደርጋል፣

12. የተቋሙን የፋይናንስ አፈጻጸም መግለጫዎችና ሪፖርቶች በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያቀርባል፣

13. የመ/ቤቱን ሂሳብ በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች ያስመረምራል፣ በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረት የማስተካከያ እርምጃ መግለጫዎች ለኃላፊ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

14. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤

15. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣

16. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤

17. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤

18. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤

19. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣ 20. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤

21. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት ይቀበላል ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣

22. በስራ ክፍሉ ተልእኮ ባለደርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣

23. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

24. በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል

 የኃላፊ ስም፡-  አቶ ጥላሁን ደምሴ

 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-54-01-85