Search

የግዥ ዳይሬክቶሬት ተግባር እና ኃላፊነት


ከዚህ ቀደም የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የነበረዉ የተቋሙን ተልዕኮ በአግባቡ መፈፀም በሚያስችል ሁኔታ ለሁለት በመክፈል ግዥ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ሆኖ ለብቻዉ የተደራጀ ሲሆን በስሩ የግዥ ቡድን ይዞ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል:-


1. ከሁሉም የሥራ ክፍሎች የአቅርቦት ፍላጎት መረጃ በማሰባሰብ የግዥ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣

2. የሚፈፀሙ ግዢዎች በመንግስት በወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣

3. ግዥ ከመፈጸሙ በፊት እቃዉ እስቶር መኖር አለመኖሩን መረጃ ይሰበስባል፣ በእስቶር የሚገኝ ከሆነ ለጠያቂዉ ክፍል ያሳዉቃል፣

4. የገበያ ጥናት ያካሂዳል፣ የተፈላጊ እቃዎች ዋጋ፣ አቅርቦትና አቅራቢ ድርጅቶችን የተመለከቱ መረጃዎች ተሰብሰበዉ እንዲያዙ ያደርጋል፣

5. ለሚገዙ ዕቃዎች ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ እና መጠን የያዘ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደረጋል፣

6. የግዥ ዘዴ በመለየት የጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል፣ ለተጫራቾች ማብራሪያ ይሰጣል፣ ጨረታ ይከፍታል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣

7. የግዥ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን ይቆጣጠራል፣ የዉል ስምምነቱን በአግባቡ የማይወጡት ላይ በህጉ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣

8. በተሰጠው የገንዘብ ውክልና መጠን መሰረት ግዥ ያጸድቃል፣ ከአቅራቢዎች ጋር ውል ይገባል፣ ግዥም ይፈጽማል፣

9. በማዕቀፍ የሚከናወኑ ግዢዉችን በመለየት ለሚመለከተዉ ተቋም በወቅቱ ይልካል፣ ግዢዉን ይከታተላል፣

10. የጨረታ አሸናፊዉ እንደታወቀ ንብረቱ ገቢ እንዲሆን ለሚመለከተዉ የስራ ክፍል ያሳዉቃል፣ የተገዛውም ዕቃ ትክክለኛና በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ገቢ መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣

11. የግዢ አፅዳቂ ኮሚቴ አስፈላጊዉን ግብዓት ያሟላል ለግዢዉ የተሟላ ሰነድና መረጃ በማቅረብ ድጋፍ ይሰጣል፣

12. የግዥ ሰነዶችን በአግባቡ ይይዛል፣ ከሚመለከታቸው ሕጋዊ አካላት ማብራሪያ ሲጠየቅ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፣

13. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤

14. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣

15. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤

16. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤

17. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤

18. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣

19. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤

20. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣

21. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካለት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ ያሳትፋል፣

22. የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤

23. በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል


     የኃላፊ ስም፡-  አቶ የዋላሽት አግዝ

     የቢሮ ስልክ ቁጥር፡-