Search

የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ /ቤት ተግባርና ሃላፊነት


የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ /ቤት የዘርፉን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች እንዲያግዝ የዘረፍ፣ የቅርንጫፍ /ቤቶች የአስተዳደር ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቡድን ይዞ በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል:-


1. ዘርፉን የሚመለከቱ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋም የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን ይደግፋል፤

2. ለጽ/ቤቱ የተመደቡ ሰራተኞች ስራ ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣

3. የዘርፉን ንኡስ ማኔጅመንት ስብሰባዎች ያቀናጃል፣ ከዘርፉ ሀላፊ ጋር በመነጋገር ለማኔጅመንት ኮሚቴ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ለይቶ ያቀርባል፣

4. የዘርፉ ኃላፊ ስትራቴጂያዊ አመራር እንዲሰጥ ለዘርፉ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያስተባብራል፣

5. በዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ውሳኔዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣

6. ለዘርፉና ከዘርፉ የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ተጠቃልለው እና ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፤

7. በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ከምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፋር ይገመገማል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣

8. የዘርፉ ሀላፊ ለሚካፈሉባቸው ብሔራዊና አለም አቀፍ ስብሰባዎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እና መግለጫዎች ተሟልተው መቅረባቸውን ያረግጣል፤

9. በዘርፉ ተፈጻሚ የሚሆኑ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎች በማዘጋጀት ለንኡስ ማኔጅመንት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፡፡

10.የዘርፉ ኃላፊ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በማይገኝበት ጊዜ ወክሎ ይሳተፋል፣ ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ንግግሮችን ያዘጋጃል፣

11.ከዘርፉ ኃላፊ የሚመሩ እና ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡ ጉዳዮች ወይም ለዘርፉ ኃላፊ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ቅሬታው ሰንሰለቱን ጠብቆ መቅረቡን ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በዘርፉ ኃላፊ ለሚወሰኑ ጉዳዮች አስተያየትና የውሳኔ ሓሳብ ያቀርባል፣

12.ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ የውሳኔ ሐሳቦች ምርምሮ ለዘርፉ ኃላፊ አስተያየት ያቀርባል፣

13.የዘርፉን ሀላፊ የስብሰባ መርሃ ግብር እና የግዜ ሰሌዳዎች ያቀናጃል፣ በዘርፉ የሚከናወኑ የጽሑፍ ግንኙነት፣ የስብሰባና የጉዞ ፕሮግራሞችን አንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸው ስራዎችን ይመራል፣

14.በዘርፉ ስር በተደራጁ የሥራ ክፍሎች መካከል ሊኖር ለሚገባውን ትስስርና መስተጋብር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያቀናጃል፣ ይመራል፣

15.በዘርፍ፣ በድሬዳዋ ቅርንጫፍ እና በቅርንጫፍ /ቤቶች ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ ይከታተላል፣ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲቀረፉ ያደርጋል፤ግብረ መልስ ይሰጣል፣

16.ከዘርፉ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመነጋገር ዘርፉ ተልዕኮ ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ የህዝብ አደረጃጀቶችንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፉበት መድረክ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣

17.ከዘርፉ ወጪ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን፣ ሰርኩላሮችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መድረሳቸዉን ያረጋግጣል፣

18.ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣

19.ሌሎች ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡


     የኃላፊ ስም፡-  አቶ ዝናቡ ቱኑ 

     የቢሮ ስልክ ቁጥር፡-