የሰው ሀብት ብቃት እና አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ተግባር እና ኃላፊነት
የሰው ሀብት ብቃት እና አስተዳደር ስራ
አስፈጻሚ ተግባራት ይኖሩታል:-
1. የሠራተኞች የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
2. አዲስ የሚቀጠሩ ሠራተኞች የስራ የማስተዋወቂያ ስልጠና (Inducation) እንዲወስዱ ያደርጋል፣
3. ብቃት ያላቸዉ ሠራተኞች ለመሳብና ያሉትን ለማቆየት የሚያስችል ስትራቴጂ በመቅረጽ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ክትትል ያደርጋል፣
4. ለተቋሙ የሚያስፈልጉ የሥራ መደቦች አይነት፣ብዛት፣ ተፈላጊ ችሎታ እና የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
5. ክፍት የሥራ መደቦችን በመለየት በደረጃ ዕድገት፣ በቅጥር፣ በዝውውር እንዲሟሉ ያደርጋል፣
6. ከስራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ባለሙያ ጋር በመሆን ምቹ የስራ አካባቢ እንዲፈጠር በቅርበት ይሰራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
7. ከሰው ሀብት አስተዳዳር ጋር የተያያዙ ዘመናዊ የአሠራር ማሻሻያ ዘዴዎችን እንዲጠኑ ያደርጋል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
8. ለተቋሙ ሰራተኞች የሚስፈልጉ ጥቅማጥቅምና ያጠናል፣ ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
9. ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን የስራ ላይ ስልጠና እንዱያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
10.ከዘርፍና ተጠሪ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሰው ሃይል ስምሪት ዙሪያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
11.በዘርፍና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሊከናወኑ የሚገባቸዉን የሰዉ ሃብት ቅጥር፣ እድገት፣ ዝዉዉር፣ ማስተዳደርና ዲሲፒሊን የሚመለከቱ ጉዳዮችን አጥንቶ ለበላይ አመራር ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ስራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
12.ሠራተኞች በተቀመጠዉ የስራ የምዘና ስርዓት መሰረት በየወቅቱ እንደመዘኑ ይከታተላል፣ ዉጤቱን ከማህደርታቸው ጋር እናዲያያዝ ያደርጋል፣
13.በዘርፉ ሀላፊ በሚሰጥ የስልጣን ዉክልና መሰረት በሰዉ ሃብት ስራ አመራርና አስተዳድር ጉዳዮች ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
14.የሠራተኞች የስራ ላይ መገኘት ሪፖርት ይሰበስባል፣ በስራ ላይ ያሉና የለቀቁትን ለይቶ በወቅቱ ለሚመለከተዉ የስራ ክፍል በፅሁፍ ያሳዉቃል፣
15.የሠራተኞችን የግል ማህደር አደራጅቶ ይይዛል፣ የመረጃ ቋት ያደራጃል፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ያዘምናል፣ ያስተዳድራል፣
16.የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
17.ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
18.የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
19.በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
20.ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
21.ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
22.ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
23.የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
24.በስራ ክፍሉ ተልእኮ የባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
25.የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
26.በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን ያከናውናል
የኃላፊ ስም፡- አቶ ንጉሴ
ተንኮሉ
የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-8
-58-31-46