Search

የሕግ አማካሪ፣ ጥቆማና ቅሬታ ማስተናገጃ /ቤት ተግባር እና ኃላፊነት


የሕግ አማካሪ፣ ጥቆማና ቅሬታ ማስተናገጃ /ቤት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን እንዲደግፍ ከተደራጀው /ቤት መካከል አንዱ ሲሆን በውስጡም የሕግ አማካሪዎችን እና የጥቆማ እና ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን በመያዝ የሚከተሉት ተግባር እና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-


1. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ስትራቴጂያዊ በሆኑ የሕግ ጉዳዮች ዙሪያ ያማክራል፤

2. ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚቀርቡ ሕግና ፍትሕን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ያስተናግዳል፣ ምላሽ ይሰጣል፣ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መቅረብ ያለባቸው ጉዳዮች ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ያደርጋል፣

3. በኢኮኖሚ እና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ በፍትሃብሄር እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ዘርፍ እና በሕግ ጉዳዮች ዘርፍ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ልዩ ትኩረትና ድጋፍ የሚሹ ስራዎች ላይ ድጋፍ ያደርጋል፣ ያማክራል፣

4. ከተለያየ አካላት የሚቀርቡ እና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጣርቶ የውሣኔ ሃሣብ እንዲቀርብ የተጠየቀባቸው ጉዳዮችን በመመርመር የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል፣

5. ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተለይቶ በተሰጠው ውክልና መሰረት ከምርመራና ክስ ጋር የተያያዙ ትእዛዝ ይሰጣል፣

6. በጽ/ቤቱ የተመደቡ አማካሪዎች፣ ዐቃብያነ ሕግ እና የአስተዳደር ሰራተኞች ያስተባብራል፣ ያሰማራል፣ የስራ አፈፃፀማቸው ይገመግማል፣ ይመዝናል፣

7. የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ እንዲሁም ዉሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ይዘረጋል፣

8. ነፃ የጥቆማና የሕግ ጥያቄ አቀባበልና ግብረ መልስ ስርዓት ይዘረጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣

9. ጥቆማ ይቀበላል፣መጣራት ያለበት ሆኖ ሲገኝ ለሚመለከታቸው ይመራል ፣አፈፃጸሙን ይከታተላል፣

10.የጽ/ ቤቱን ተልዕኮ ለማሳካት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙም ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

11.ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ህጎች ለመቅረጽ ግብአት የሚሆኑ ምክረሃሳቦች ያቀርባል፤

12.ለጽ/ቤቱ የሚስፈልገው ሰብአዊና ቁሳዊ ፍላጎት/ግባት እንዲሟላ ያደርጋል፣ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉንም ያረጋግጣል፣

13.አማካሪዎችና ሌሎች የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በሥነምግባር እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈጸምም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፣

14.የጽ/ቤቱን መረጃዎችና ምርጥ ተሞክሮዎች ያደራጃል፣

15.ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ሰንሰለቱን ጠብቆ መቅረቡን ያጣራል፣ ምላሽ ይሰጣል፣ ወይም በሕግ መሰረት በሚመለከታቸው አካላት እንዲፈታ ይመራል፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፣ የተሰጡ ውሳኔዎች አፈፃፀም ይከታተላል፣

16.ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

  የኃላፊ ስም፡- አቶ ምስክር ታሪኩ 

  የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-8-54-70-99