በኢፌዴሪ
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተግባር እና ኃላፊነት
ጽ/ቤቱ እንደአካል ተጠሪነቱ ለፍትሐብሔር እና ልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዘርፍ ሆኖ
በስሩ የወንጀል ጉዳዮች፣ የፍትሐብሔር ጉዳዮች፣ የጥብቅና ክትትል እና አስተዳደር ጉዳዮች፣ የሴቶች እና ሕጻናት፣ የመዝገብ አያያዝ
እና አስተዳደር ቡድን እና የአስተዳደር እና ፋይናንስ ማስተባሪያን የያዘ ነው፡፡
የጽ/ቤቱ ተግባር እና ኃላፊነት
1. የተቋሙንና የዘርፉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ
የስራ ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፣ አፈፃጸማቸውን ይከታተላል ፣ድጋፍ ይሰጣል፤
2. ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልገውን ሰብአዊ እና
ቁሳዊ ግብአት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
3. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች
እንዲዘጋጁ እና እንዲሻሻሉ ሀሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ መሠረት መፈጸማቸውን ይከታተላል፤
4. በስራ ክፍሉ ያሉትን ሰራተኞች በስነምግባር
እንዲገነቡ ያደርጋል፣ ጥሰት ሲፈፀም ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
5. በስራ ክፍሉ ያሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት
ለይቶ አቅማቸው የሚገነባበትን ስልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ ያደርጋል፤የስራ ክፍሉን ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም ይመዝናል፤
6. ከዘርፉ ኃላፊ ጋር በመመካከር ለስራ ክፍሉ
ተልእኮ መሳካት አስተዋፅኦ ካላቸው ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ በቅንጅት ይሰራል፤
7. ከስራ ክፍሉ ተልእኮ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን
እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ያደራጃል፣
8. ለስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን
ተቀብሎ ያስተናግዳል ፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤ 9. የስራ ክፍሉን የስራ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡዱኖች ሪፖርት
ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
10. በስራ ክፍሉ ተልእኮ የኅብረተሰብ ክፍሎች
የሚሳተፉበት የሕዝብ መድረክ ያዘጋጃል፣ያሳትፋል፣
11. የስራ ክፍሉን የሚመለከቱ ምርጥ ተሞክሮዎችን
እንዲቀመር ያደርጋል፤
12.የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች
መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣
13. በተጨማሪም ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ተግበራትን
ያከናውናል
የቡድኖች የወል ተግባርና ኃላፊነት
1. የስራ ክፍሉን ዕቅድ መነሻ
በማድረግ የቡድኑን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለአፈፃፀሙ ከትትልና
2. ለቡድኑ የሚያስፈልገውን
ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግብዓት እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፤
3. ለቡድኑ አባላት የስራ
ስምሪት በመሰጠት የተሰጣቸውን ስራ በጥራት፣ በተቀመጠው ጊዜ እና በህጉ መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፣ የስራ አፈፃፀማቸውን ይመዝናል፤
4. ለቡድን ስራ ውጤታማነት
የውይይትና የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮች ያዘጋጃል፣
5. የቡድኑ አባላት መካከል
ጠንካራ የቡድን ስሜት እንዲፈጠር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ የማብቃት (Coaching) ሥራ ያከናውናል፤
6. የቡድኑን አባላት የክህሎት
ክፍተት ይለያል፣ ስልጠና እንዲያገኙ ያመቻቻል፤
7. የቡድኑ አባላት የእርስ
በእርስና የግል አቅም ግንባታ ዕቅድ (self-development plan) እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፣ በዕቅዱ መሰረት ስለመፈፀሙ ይከታተላል፣
ግብረ መልስ
8. የቡድኑ አባላት የስነምግባር
ሁኔታ ይከታተላል፣ የስነምግባር ጉድለቶች የሚያሳዩ የቡድኑ አባላት እንዲታረሙ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጠያቂነት እንዲሰፍን
9. ከቡድኑ ተግባርና ኃላፊነት
ጋር የተያያዙ መረጃዎች ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
10. ለቡድኑ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን
እና ቅሬታዎችን ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
11. የቡድኑን የስራ አፈፃፀም
ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ከቡድን አባላት ሪፖርት ይቀበላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
12. የቡድኑን የስራ አፈጻጸም
ሪፖርት በወቅቱ ለስራ ክፍሉ ያቀርባል፣
13. ምርጥ ተሞክሮዎችን ይለያል
እንዲቀመር ያደርጋል፤
14. ከስራ ክፍሉ የሚሰጡ
ሌሎች ተግበራትን ያከናውናል፤
1.
የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ቡድን
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወሰን የሚፈጸሙ እንዲሁም የፌዴራል የወንጀል ስልጣን ስር
የሚወድቁ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ላይ ክትትል የሚደረግ ሲሆን፣ በዚህም ምርመራን መምራት፣ ተገቢውን ህጋዊ ውሳኔ የምርመራ መዝገብ
ላይ መሰጠት፣ በሕግ አግባብ የጥፋተኝነት ድርድር የማድረግ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቀጥታ ክስ፣ የይግባኝ እና የሰበር አቤቱታዎችን
የማቅረብ እና ክርክር የማድረግ፣ በሙስና ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ማስመለስ እና ማስወረስ፣ በጽ/ቤቱ በሚታዩ የሙስና
ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ስለመርዳት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር፣ የገንዘብ ቅጣትን
ማስፈጸም አጠቃላይ የመዛግብት አፈጻጸምን የመገመገም እና የተጠናቀረ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ የማቅረብ እንዲሁም ከሙስና ወንጀል
ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጋር በሚኖር የክትትል እና ድጋፍ ስራ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው (focal person) ይኖረዋል፡፡ የመዛግብት ምርመራ እና ክርክር ስራዎችን በቡድኑ የሚገኙ ዐቃብያነ ሕግ የሚያከናውኑ
ሲሆን የቡድን አስተባባሪ ደግሞ አጠቃላይ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ የቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን
የሙስና ወንጀል መዛግብት አፈጻጸም እንደየወንጀሉ አይነት የተጠናቀረ እና የተገመገመ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣
2.
የኢኮኖሚና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ቡድን
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወሰን የሚፈጸሙ እንዲሁም የፌዴራል የወንጀል ስልጣን ስር
የሚወድቁ የኢኮኖሚ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ክትትል የሚደረግ ሲሆን፣ በዚህም ምርመራን መምራት፣ ተገቢውን ህጋዊ ውሳኔ የምርመራ መዝገብ
ላይ ውሳኔ መሰጠት፣ በሕግ አግባብ የጥፋተኝነት ድርድር የማድረግ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቀጥታ ክስ፣ የይግባኝ እና የሰበርአቤቱታዎችን
የማቅረብ እና ክርክር የማድረግ፣ በኢኮኖሚ ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ማስመለስ እና ማስወረስ፣ በጽ/ቤቱ በሚታዩ የኢኮኖሚ
ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ስለመርዳት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር፣ የገንዘብ ቅጣትን
ማስፈጸም አጠቃላይ የመዛግብት አፈጻጸምን የመገመገም እና የተጠናቀረ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ የማቅረብ እንዲሁም ከዳይሬክቶሬቱ ጋር
በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው (focal person) በመሆን ያለግላል፡፡ የመዛግብት ምርመራ እና ክርክር ስራዎችን በቡድኑ የሚገኙ ዐቃብያነ ሕግ የሚያከናውኑ
ሲሆን የቡድን አስተባባሪ ደግሞ አጠቃላይ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ የቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን
የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች አፈጻጸም የተጠናቀረ እና የተገመገመ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣ ከኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ ግንኙነት ላይ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው ይሆናል፡፡
3.
የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ቡድን
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወሰን የሚፈጸሙ እንዲሁም የፌዴራል የወንጀል ስልጣን ስር
የሚወድቁ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ክትትል የሚደረግ ሲሆን፣ በዚህም ምርመራን መምራት፣ ተገቢውን ህጋዊ
ውሳኔ የምርመራ መዝገብ ላይ ውሳኔ መሰጠት፣ በሕግ አግባብ የጥፋተኝነት ድርድር የማድረግ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቀጥታ ክስ፣
የይግባኝ እና የሰበር አቤቱታዎችን የማቅረብ እና ክርክር የማድረግ፣ በተደራጁ እና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ማስወረስ
እና ማስመለስ፣ በጽ/ቤቱ በሚታዩ የተደራጁ እና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ
እና ስለመርዳት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር፣ የገንዘብ ቅጣትን ማስፈጸም የጸረ-ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ከስደት
ተመላሾች መርዳት እንዲሁም የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ስራዎች፣ አጠቃላይ የመዛግብት አፈጻጸምን የመገመገም እና የተጠናቀረ
ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ የማቅረብ እንዲሁም ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው
(focal person) በመሆን ያገለግላል፡፡ የመዛግብት ምርመራ እና ክርክር ስራዎችን በቡድኑ የሚገኙ ዐቃብያነ ሕግ የሚያከናውኑ
ሲሆን የቡድን አስተባባሪ ደግሞ አጠቃላይ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡የቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን የተደራጁ
እና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀል ጉዳዮች አፈጻጸም የተጠናቀረ እና የተገመገመ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣ ከተደራጁ እና ድንበር
ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ ግንኙነት ላይ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው ይሆናል፡፡
4.
የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ቡድን
በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዙሪያ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወሰን የሚፈጸሙ እንዲሁም
የፌዴራል የወንጀል ስልጣን ስር የሚወድቁ የልዩ ልዩ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ክትትል የሚደረግ ሲሆን፣ በዚህም ምርመራን መምራት፣
ተገቢውን ህጋዊ ውሳኔ የምርመራ መዝገብ ላይ ውሳኔ መሰጠት፣ በሕግ አግባብ የጥፋተኝነት ድርድር የማድረግ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች
በተሰጠው ስልጣን ልክ የቀጥታ ክስ፣ የይግባኝ እና የሰበር አቤቱታዎችን የማቅረብ እና ክርክር የማድረግ፣ በልዩ ልዩ ወንጀሎች የተገኘ
ገንዘብ ወይም ንብረት ማስወረስ እና ማስመለስ፣ በጽ/ቤቱ በሚታዩ የልዩ ልዩ ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ
ማቅረብ እና ስለመርዳት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር፣ የገንዘብ ቅጣትን ማስፈጸም አጠቃላይ የመዛግብት አፈጻጸምን የመገመገም እና
የተጠናቀረ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ሃላፊ የማቅረብ እንዲሁም ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው
(focal person) በመሆን ያገለግላል፡፡ የመዛግብት ምርመራ እና ክርክር ስራዎችን በቡድኑ የሚገኙ ዐቃብያነ ሕግ የሚያከናውኑ
ሲሆን የቡድን አስተባባሪ ደግሞ አጠቃላይ የክትትል እና የድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ የቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን
የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች አፈጻጸም የተጠናቀረ እና የተገመገመ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣ ከልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ ግንኙነት ላይ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው ይሆናል፡፡
5.
የመዝገብ አያያዝ አስተዳደር ቡድን
1. ተንቀሳቃሽ፣ ውሳኔ ያገኙና የአስተዳደር መዝገቦችን
የማደራጀት፣ የማስተዳደርና፣ የመቆጣጠር፤ የችሎት መዝገቦች ሪከርድና መረጃ አያያዝና አሰራር በሚመለከት በየጊዜው የሚወጡ ደንቦች፣
መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶች በአግባቡ መተግበራቸውን ተከታትሎ ያረጋግጣል፡፡
2. ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ሚስጥራዊ ሪከርዶችና
ሰነዶች የመለያ ኮድ እንዲዘጋጅላቸውና ተገቢውን የአያያዝ ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያገኙ እና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከተገልጋዮች
የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ምላሽ ይሰጣል፡፡
3. ከልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶች እና የተቋሙ የስራ
ክፍሎች ወደ ጽ/ቤቱ ደብዳቤዎች ሲደርሱ የደብዳቤዎቹ አድራሻ ለጽ/ቤቱ መሆኑን አረጋግጦ፣ የተጠቀሱ አባሪዎች ካሉ በትክክል ተያይዘው
መላካቸውን አጣርቶ ፈርሞ መቀበል እንዳመጣጣቸው እየመረመረ ወደሚመለከተው ክፍል/ኃላፊ ይመራል፣
4. ከጽ/ቤቱ ወጪ የሚደረጉ የጽሑፍ መልእክቶችና
ደብዳቤዎች ስልጣን በተሰጠው ኃላፊ/ባለሙያ የተፈረሙ መሆናቸውን፣ እንደዚሁም መሟላታቸውን እያረጋገጠ ማህተም ያደርጋል፡
5. የማይንቀሳቀሱ መዛግብትን ለይቶ ለሚመለከተው
አካል የማዘዋወር የሚወገዱትንም ለይቶ ዝርዝር በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
6. ወጪ ደብዳቤዎች
በተዘረጋው የሪኮርድ ሥርዓት መሠረት ትክክለኛው ኮድና መለያ ቁጥር የተሰጣቸው መሆኑንና የቀረውም በትክክለኛው ማህደር ውስጥ ፋይል
መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፡፡
6.
የሴቶችና ህፃናት ፍትህ እና የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ቡድን
በጽ/ቤቱ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያጣራ እና ተገቢውን
ህጋዊ ውሳኔ የሚሰጥ፣ በፍርድ ቤት ክሶችን በማቅረብ ተገቢው ህጋዊ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚያደርግ እንዲሁም ስነልቦናዊ ድጋፍን የሚሰጥ
ዐቃብያነ ሕግን እና የስነልቦና ባለሞያን የያዘ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የሚያከናውናቸው ተግባራት፡-
1. ቡድኑ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ያሉ ሴቶችና ሕፃናት
በተመለከተ የሚሰሩ ስራዎችን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣
2. በፍትህና እንክብካቤ ማእከላት የሚሰጡ አገልግሎቶች
ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን ይለያል፣ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ እና በሴቶች እና ህጻናት ላይ የመፈጸሙ ወንጀል
ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፣
3. በህፃናት ላይ የሚፈፀሙና ከሴቶች ጾታዊ ጥቃት
ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የመረጃ ስርዓት መሰረት መረጃ ይይዛል፣ ይተነትናል፣ ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርት ለጽ/ቤቱኃላፊ እና በሴቶች
እና ህጻናት ላይ የመፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፣
4. በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን
ለመከላከል የሚያስችል የንቃተ ሕግ ስራ ለህብረተሰቡ ይሰጣል፤
5. የተቋሙ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ በጽ/ቤቱ
ተካቶ እንዲፈጸም ያደርጋል፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣
6. የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ የባለብዙ ዘርፍ
በተግባራት በዕቅዶች ተካተው እንዲፈፀሙ ይከታተላል፣
7. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኛ
እና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካላት ምቹ መሆኑን ያረጋግጣል፣
8. የባለብዙ ዘርፍ ተግባራት በጽ/ቤቱ ዕቅድ
ስር እንዲካተት ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
9. የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ በጽ/ቤቱ
የተከናወኑ ስራዎችን መረጃ ያደራጃል ለሴቶች፣ ህጻናት እና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክቶሬቱ ይልካል፣
7.
የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ቡድን
1.
ለአቅመ ደካማ ዜጎች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ የሕግ ምክር ይሰጣል
2.
የአቅመ ደካማ ዜጎችን ፍትሐብሔራዊ መብት ለማስከበር አቅመ ደካማ ዜጎችን ወክሎ ድርድር ያደርጋል፣ በድርድሩ መሰረት ስምምነት ላይ
ሲደረስ በስምምነቱ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ያስፈጽማል
3.
አቅመ ደካማ ዜጎችን ወክሎ ስልጣን ባለቀው ፍርድ ቤት አግባብነት ያለውን የክስ ማመልከቻ/መልስ ያዘጋጃል፣ ክሶች በፍርድ ቤት ያስከፍታል፣
በቀጥታ ክስ፣ በይግባኝ እና በሰበር ተገቢውን ክርክር ያደርጋል፣ የተሰጡ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ያስፈጽማል፡፡
4.
በድሬዳዋ የሚገኙ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ መ/ቤቶች የሚገቧቸው ውሎችን ይመረምራል፣ ያዘጋጃል፣ ተገቢው ድጋፍ ይሰጣል፣
5.
በድሬዳዋ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
6.
የጽ/ቤቱን የፍትሐብሔር አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር
ጉዳይ ዙሪያ ለሚኖር የክትትል እና ድጋፍ ስራ የጉዳይ ሰው (focal person) በመሆን ያገለግላል፡፡
7.
የቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን የፍትሐብሔር ጉዳዮች አፈጻጸም የተጠናቀረ እና የተገመገመ ሪፖርት ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣
ከፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በሚኖረው የክትትል እና ድጋፍ ስራ ግንኙነት ላይ የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው ይሆናል፡፡
8.
በድሬዳዋ የሚገኙ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች በፌዴራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት
የሚወጡ መመሪያዎች ወደ ፌዴራል ህግ አፈጻጸም ክትትል ዳይሬክቶሬት እንዲላክ ማድረግ፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባሉ የመንግስት
መስሪያ ቤቶች የፌዴራል ህጎች ተፈጻሚነትን ያረጋግጣል፣
9.
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጡ የጠቋሚዎች እና ምስክሮች ጥበቃ አገልግሎቶችን ያስተባብራል፣ ተገቢው የስራ አቅጣጫ ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ያቀርባል፣
አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ከወንጀል ጠቋሚዎች እና ምስክሮች ጥበቃ ዳይክቶሬት ጋር በሚኖር የክትትል እና ድጋፍ ስራ ግንኙነት ላይ
የጽ/ቤቱ የጉዳይ ሰው ይሆናል፡፡
8.
የአስተዳደርና ፋይናንስ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቡድን
1. ለለፅቤቱ የሚያስፈልገውን በጀት በማስፈቀድ
የስራ እቅድ ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
2. የቡድኑን አባላት የአሰራር ክፍተት በመለየት
ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል
3. የግዥ እቅድ በማዘጋጀትና በማጽደቅ በተመረጡ
የግዥ ዘዴዎች ግዥዎች እንዲፈጸሙ በማድረግ ንብረቱ ለተጠቃሚ አካል እንዲደርስ ያደርጋል
4. የሂሳብና የግዥ እና የንብረት ወርሃዊ የሩብ
ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርቶቸችን ያስተላልፋል
5. የክፍያ ጥያቄዎች ሲቀርቡ ለሚመለከተው ባለሙያ
ያስተላልፋል፡፡
6. ከአገልግሎት ውጭ ስለሆኑ ንብረቶች አወጋገድ
እያጠና ለዋና ተቋም ሪፖርት ያቀርባል፣
7. ተገቢው የንብረት ገቢ፣ ወጪና ዝውውር መከታተያና
መቆጣጠሪያ መዝገቦችና ካርዶች መያዛቸውን ያረጋግጣል፡፡
8. የቋሚና የአላቂ ዕቃዎች መዝገብ እንዲያዝ
ያደረጋል የዕቃዎች ገቢ ወጪና ዝውውር በዓይነት በስም በመጠንና በዋጋ ተለይተው መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፣ የክምችት ዕቃዎችን ከወጪ
ቀሪ ተቀናንሶ እንዲያዝ በማድረግ የዕቃዎችን የክምችት መጠን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
9. የግዢ እቅድ በማዘገጀት፤ ግዥዎች በዋጋ ማቅረቢያ
የግዥ ዘዴ መመሪያን በመከተል እንዲከናወኑ ያደርጋል፡፡
10. ግዢዎች በቀረበው ጥያቄና ስፔስፍኬሽን መሰረት
መፈጸማቸውን በመከታተል ያስፈጽማል፡፡
11. የተገዙ እቃዎች በጥያቄው መሰረት የንብረት
ስርጭት ያደርጋል፣ ንብረቶችን መዝግቦ መያዝና የንብረት መለያ ኮድ መሰጠቱንም ይከታተላል፡፡
12. እቃዎቹ ከስቶር ከማለቃቸው በፊት እንዲተኩ
ክትትል ያደርጋል፡፡
13. ክፍያ የተፈጸመባቸውን የሂሳብ ሰነዶች በማደራጀት
እና የሂሳብ ምዝገባ በማካሄድ ለፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፡፡
14.የሰው ሀይል ፍላጎት በመለየት እንዲሟላ ለዐቃብያነ
ሕግ አስተዳዳር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት እና ለሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ጥያቄ ያቀርባል፣ ሂደቱን ይከታተላል፣
15.በተጨማሪ ሌሎች በጽ/ቤቱ ሀላፊ የሚሰጡ አስተዳደራዊ
ጉዳዮችን ይከታተላል ያስተባብራል፡፡
16.የቡድኑን ወቅታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት
ለቅርብ ኃላፊው ያቀርባል፡፡
9.
የዐቃቤ ሕግ አስተዳደር ንዑስ-ጉባዔ
1. የድሬዳዋ ዐቃብያነ ሕግን የመረጃ ቋት ያደራጃል፣ያስተዳድራል፣የዐቃቤያነ
ሕግን የግል ማህደር አደራጅቶ ይይዛል የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ያዘምናል፣
2. ለዐቃብያነ ሕግ የተሠጡ ቤቶችንና መረጃ አደራጅቶ
ይይዛል፣ሲለቁ ለተቋሙ መመለሳቸዉን ያረጋግጣል፣
3. የዋና ጉባኤውን ውሳኔ የማይጠይቁ የዐቃቤያን
ሕግ የድጋፎችና ዕለታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣
4. በድሬዳዋ የተመደቡ ዐቃብያነ ሕግ ሙያዊ ስነምግባርን
ይከታተላል፣ የሙያዊ ስነምግባር ላይ ስልጠና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲሰጥ ያደርጋል
5. በደንቡ መሰረት በቅርጫፍ ፅ/ቤቱ በዐቃብያነ
ሕግ የሚፈፀሙ ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶችን በማየት እልባት ይሰጣል፤
6. ሌሎች በዋና ጉባኤ የሚሰጡትን ተግባር እና
ኃላፊነት ይወጣል፡፡
10.
የጥብቅና አስተዳደር እና ነጻ የሕግ ድጋፍ ቡድን
5. በድሬዳዋ የሚገኙ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የጥብቅና
ፈቃድ ያወጡ ጠበቆችን አመታዊ የፈቃድ እድሳት ያደርጋል፣
6. በድሬዳዋ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍቃድ ያላቸው
ጠበቆች የአገልግሎት አሰጣጥ እና ስነምግባር ክትትል ያደርጋል፣
7. ለጠበቆች የስነ-ምግባር ስልጠና ይሰጣል፣
8. በድሬዳዋ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍቃድ ያላቸው
ጠበቆች የሚፈጽሟቸውን የስነስርዓት ግድፈት በማጣራት ለዋና የጠበቆች የስነ ምግባር ጉባኤ ያቀርባል፣
የኃላፊ ስም፡-
የቢሮ ስልክ ቁጥር፡-