Announcement
Next →

ለሁሉም የሚዲያ አካላት

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክቡር አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መ/ቤት መስብስቢያ አዳራሽ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በመከላከያ ጄኔራሎች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ አንድሁም ስለተቋሙ ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴ አሰመልክቶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣሉ።

ስለሆነም የሚዲያ አካላት በቦታው ተገኝታችሁ እንድትዘግቡ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118547189 ደውላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳስቢያ : ወደ ተቋሙ ስትመጡ የሚዲያ ተቋም የሥራ ባልደረባ መሆናችሁን የሚገልጽ መታውቂያ ይዞ መምጣት የግድ የሚል መሆኑን እናሳውቃለን።


about 3 years ago