Next →
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ በዐቃቤ ሕግ ደረጃ-II እና በጀማሪ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ-I መደብ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ታኅሣሥ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ (እስከ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም.) በተወዳዳሪነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
1. አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች
1.1. ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና በኢትዮጵያ የሚኖር የምትኖር ፤
1.2. ለሕገ መንግስቱ እና ለሕግ የበላይነት ተገዢ የሆነ/የሆነች ፤
1.3. የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች ፤
1.4. በታታሪነቱ/ቷ ፣ በታማኝነቱ/ቷ ፣ በሥነ-ምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች መሆኑን/ኗን ይ/ትሰራበት ከነበረው ተቋም ማቅረብ የሚችል /የምትችል ፤
1.5. የወንጀል ቅጣት ሪከርድ የሌለበት/ባት ፤
1.6. የፌዴራል መንግስቱን የሥራ ቋንቋ የሚችል/የምትችል ፤
2. ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ
2.1. ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ከ2008ዓ.ም ወዲህ የተመረቀ /የተመረቀች ፤ የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) ለወንድ 3.5 ፣ ለሴት 3.25 ፣ ለአካል ጉዳተኛ ወንድ 3.25 ፣ ለአካል ጉዳተኛ ሴት 3.00 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት ፤
2.2. የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ማለፊያ ነጥብ እና ከዚያ በላይ በማምጣት ፈተናውን ያለፈ/ያለፈች ፤
3. በፌዴራል ዐቃቤ ሕግነት ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት፤
4. የሥራ ልምድ፡- በዐቃቤ ሕግነት፣ በዳኝነት፣ በጥብቅና ወይም በሕግ መምህርነት ቢያንስ
4.1. ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ-II በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ 3 (ሶስት) አመት ወይም በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ 0 (ዜሮ) አመት ፤
4.2. ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ-I በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ 5 (አምስት) ወይም በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ 2 (ሁለት)ዓመት ፤
5. ተፈላጊ ብዛት፡- ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ-II - 40 (አርባ) እና ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ-I – 10 (አስር)
6. እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰጠውን የጽሁፍም ይሁን የቃል ወይም ሁለቱንም ፈተና ማለፍ የሚችል /የምትችል
7. የሥራ ቦታ፡- የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሆኖ ተቋሙ በሚመድብበት የትኛውም የሥራ ቦታ ወይም ሥራ ክፍል መስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች
8. ደመወዝ፡- በተቋሙ ስኬል መሰረት ፤
9. የምዝገባ ቦታ፡- በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ ጽ/ቤት ፤
10. አድራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፣ ወረዳ 08 ፣ ጆሞ ኬንያታ ጎዳና ፣ ከባንቢስ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ በአካል ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይቻላል።
በተጨማሪም https://forms.gle/gsVXMso8EnAsPEvc9 በዚህ ሊንክ መረጃ በመሙላት እና ማስረጃዎችን በማያያዝ መመዝገብ ይቻላል፡፡
11. የምዝገባ ቀን፡- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ፤
12. ከተቀመጠው ዝቅተኛ የመመረቂያ ነጥብ፣ የመወጫ ፈተና ውጤት እና የትምህርት ደረጃ በላይ ያላቸው አመልካቾች ይበረታታሉ።
ማስታወሻ፡- ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገባቸው ሰነዶች፡-
1. ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ/ፓስፖርት ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ፤
2. ይሰራበት ከነበረው መስሪያ ቤት የተጻፈ የሥነ-ምግባር ማስረጃ ፤
3. ዋና የትምህርት ማረጃቸውን እና የሥራ ልምድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ፤
ለበለጠ መረጃ ፡-
በስራ ሠዓት በስልክ ቁጥር ፡- +251115157432 ላይ በመደወል ፤ እንዲሁም በኢሜል አድረራሻ፡- mojpublicprosecutorsa@gmail.com ላይ በመፃፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://forms.gle/gsVXMso8EnAsPEvc9
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር