Search

የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል ዳይሬክቶሬት


ይህ ዳይሬክቶሬት የዴሊቨሮሎጂ (የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት) ስራን ከለውጥ ስራዎች እና ከፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም ጋር በአንድ ላይ የሚመራ ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ ውስጥ  የዴሪቨሮሎጂ ማስተባበሪያ፣ የለውጥ ስራዎች ማስተባበሪያ እና የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ተብለው ተደራጅተዋል፡፡ ተግባርና ኃላፊነቶቹም፡-

 

የዴሊቨሮሎጂ ማስተባበሪያ (Delivery Unit)

 

ይህ የስራ ክፍል በዋናነት ተቋሙ የቅድሚያ ትኩረት የሚያደርግባቸውን የተመረጡ የአፈጻጸም ጉዳዮች በጥናት ይለያል፣

 

የተለዩ የአፈጻጸም ጉዳዮችን የአፈጻጸም ደረጃ (Standards) ይለያል፣

 

የተለዩ የአፈጻጸም ውጤቶችን በአጭር ጊዜ ለማሳካት የሚያስችሉ ዝርዝር የአሰራር እና የአፈጻጸም መፍትሔዎችን በጥናት ይለያል፣

 

የተለዩ የአፈጻጸም ድክመቶችን እና ምክንያቶቻቸውን በመለየት የተዘጋጁ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ከበላይ አመራሩ ጋር በመሆን በትክክል ተግባራዊ እንዲደረጉ ያደርጋል፡፡

 

በለውጥ አመራር ማስተባበሪያ

 

የለውጥ ስራዎችን በብቃትና በትጋት ሊመራና ሊተገብር የሚችል አስተማማኝ የሆነ የሰው ሀይል የሚፈራበት ስርአት ከሚመከታቸው አካላት ጋር በመሆን መዘርጋት፣

 

የለውጥ ስራዎች የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ አሰራር ዕውን ለማድረግ እና ለማሳካት በሚያስችል ሁኔታ የሚተገበሩበት ስርአት መዘርጋት፣

የለውጥ ስራዎች በተቀናጀና በተዋሀደ አሰራር እንዲሁም በሚቀመጥላቸው የአፈጻጸም ደረጃ ለመተግበር የሚያስችላቸው ድርጅታዊና ቴክኒካዊ ብቃት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣

 

በለውጥ ስራዎች ውስጥ ህብረተሰቡ በስፋት የሚሳተፍበትን፣ በስራዎቹ አስፈላጊነትና ጥቅሞች ላይ ከውጭና ከውስጥ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል የአሰራር ስርአት ከሚመለከታቸው ሌሎች  አካላት ጋር በመሆን መዘርጋት፣

 

በመስሪያ ቤቱ ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመሰብሰብ፣ ለመቀመርና ለማስፋፋት የሚያስችል አስራር ስርአት በመዘርጋት መተግበር፣

 

ለፍትህ ስርአቱ መሻሻልና መጎልበት አስተዋጾ የሚያበርክቱ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች፣ የቴክኒኮችና የቴክኖሎጂ ስራዎች የሚበረታቱበት ከእነዚህ ስራዎችም ተቋሙ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበትን አሰራር ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በማጥናት ተግባራዊ ማድረግ፣

 

ከለውጥ ስራዎች የሚገኙ ውጤቶችን እና የለውጥ ሂደቶችን ለመከታተል፣ ለመገምገም፣ የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ እና የማቋርጥ ተቋማዊ መሻሻልን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ወጥ የሆኑ ስትራቴጂያዊ፣ ተቋማዊ፣ ቡድናዊና ግለሰባዊ የስራ አፈጻጸም መመዘኛ ስርአቶችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በማዘጋጀት ተግባራዊ የሚሆኑበትን የአሰራር ስረአት መዘርጋት፣

 

በመስሪያ ቤቱ የሚሰሩ የለውጥ ስራዎችን አስመልክቶ ከሌሎች ጋር በሚደረጉ የትብብርና የእርዳታ ግንኙነቶችን በባለቤትነት ማቀድ፣ መምራት፣ ማስተባበርና ተፈጻሚነታቸውን መከታተል፣

 

በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን ጨምሮ የወንጀል ፍትህ ስርአቱን ለማሻሻልና ለመለወጥ ተብሎ ከሚሰሩ ስራዎች ጋር ተያይዞ የሚገኙ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣ መተንተን እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት ናቸው፡፡

 

ፍትህ ስርአት ማሻሻያ ማስተባበሪያ

 

በወንጀል፣ በፍትሐብሄር እና በሌሎች ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ማካሄድ

 

በጥናት በተለዩ ጉዳዮች ላይ በመመስረት በፍትህ ስርዓት ለማሻሻል የሚከናወኑ የፕሮጀከት መቅረጽ፣

 

የፕሮጀክቶች አተገባበር ውጤታማነት ላይ ግምገማ ማድረግ፣

 

በማሻሻያ ፕሮግራሙ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶችና ሌሎች ጉዳዮች የዕቃና የአማካሪ ግዥዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን መፈጸምና ማስተላለፍ፣

 

ህግ ረቂቅና ማሻሻያ ስራዎችን ከብሔራዊ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪምክር ቤት ጋር እና ከህግ ማርቀቅና ማስረጽ የስራ ሂደት ጋር በመሆን ማከናወን ናቸው፡፡


የኃላፊ ስም፡- አቶ በረከት ማሞ


የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-54-03-82