Search

የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት

አደረጃጀት


ዚህ ዳይሬክቶሬት ሦስት ማስተባበሪያዎች የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-

የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች መከታተያ ማስተባበሪያ፣

ክርክርና ፍርድ ማስፈፀም ጉዳዮች ማስተባበሪያ፣ እና

ዓለም አቀፍና የድርድር ጉዳዮች ማስተባበሪያ


የዳይሬክቶሬቱ ተግባርና ኃላፊነት


መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ ያደርጋል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

 

በግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች የውል ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያደርጋል፣ የሕዝብና የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤

 

የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤትን በመወከል የፍትሐ ብሔር ክስ ይመሰርታል፤ በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር ያደርጋል፤ በተጀመረ ክርክር ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ ይከራከራል፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣ በሕግ መሠረት ፍርድን ያስፈፅማል፤

 

የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸዉ ያልተግባቡባቸው የፍታሐ ብሔር ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ ይሰጣል፤ በውሳኔው መሰረት መፈፀሙን ያረጋግጣል፤

 

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ ይከራከራል፤


የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐ ብሔር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም ይደራደራል፤

 

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በዓለምአቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከስበት ወይም በሚከሰስበት ጉዳይ መንግስትን በመወከል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ክርክር ያደርጋል፤ ድርድር ያካሂዳል፤ ውሳኔውንም ያስፈፅማል፤

 

 የኃላፊ ስም፡-  አቶ ምስክር ታሪኩ

 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-26-58