Search

  የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


በዚህ የስራ ሂደት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 

የዳይሬክቶሬቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ የተለያዩ የግዢ ውሎችን በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው ጋርይፈራረማል፣

 

በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት የማይሰጡ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች እንዲለዩ በማድረግ ባለው የመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት ወቅታዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡

 

የቋሚ ንብረት መዝገብ በአግባቡ መያዙን ንብረቶች መለያ ቁጥር አግኝተው መመዝገባቸውን ቋሚና አላቂ ንብረቶች በንብረት ሥራ አመራር ደንብና መመሪያዎች መሠረት ገቢና ወጪ መደረጋቸውንና ለተፈለጉ ዓላማዎች መዋላቸውን ያረጋግጣል፡፡

 

የግዥና ንብረት አስተዳደር ውሳኔዎችን ከመንግሥት ደንብና መመሪያ አንፃር መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

 

የኬዝ ቲም አስተባባሪዎችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም በሥሩ ላሉ ክፍሎች ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡


 የኃላፊ ስም፡-  አቶ ኤፍሬም ዓለሙ


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-58-02-60