Search

የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት


ይህ ዳይሬክቶሬት ከምስክሮች፣ ከጠቋሚዎች እና ከሌሎች አካላት የሚቀርቡ የከለላና የጥበቃ ማመልከቻዎችን ተቀብሎ በተዘረጋው አሰራር ስርዓት መሰረት የሚያስተናግድ ሲሆን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነቱም፡-


ከተጠቃሚ አመልካች፣ ፖሊስ፣ ከዐቃቤ ህግ ወይም እና ከሌሎች አካላት የሚመጡ የጥበቃ ተጠቃሚማመልከቻዎችን ይቀበላል፡፡

 

በጥበቃ ተጠቃሚ የሚነሱ የጥበቃ ጥያቄዎችን ለማስተናገድእንዲቻል በተለይምበምስክር/ጠቋሚው ላይየተጋረጠበት ከባድ አደጋ ስለመሆኑ ለመመዘን የሚረዱእንዲሁም በአስቸኳይ የምስክሮች ጥበቃ ስር ከለላ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝርዝር መመዘኛዎችን ያዘጋጃል፡፡

 

የአደጋ ሁኔታዎችን ከሚመለከተው አካል ወይም ቦታ በማጠራት ቀድሞ ጊዚያዊ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ለምስክሮች ጥበቃ ዋና ክፍል አስተያየት ያቀርባ፡፡

 

ከተለያ አካላት በምስክርና ጠቋሚዎች የአደጋ ስጋት ላይ የሚቀርቡ ስጋቶችን ሪፖርት በመሰብሰብ ይተነትናል ሕብረተሰቡና ሌሎች አካላት የአደጋ ስጋት ላይ መረጃ በግልጽ የሚሰጡበትን መንገድ ያመቻቻል፤

 

በፌዴራልና በቅርጫፍ ለጥበቃ ተጠቃሚነት የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ላይ የቀረበው የአደጋ ስጋት ለጥበቃ ተጠቃሚነት የሚያበቃ ስለመሆኑ አስተያየቱን ውሳኔ ለሚሰጠው ኮሚቴ ያቀርባል፤

 

ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ከጠየቁት የጥበቃ አይነቶች አንዱን ወይም በተደራቢ ወይም ለስጋቱ ተገቢ መስሎ የታየውን በመመዘን ከጥበቃ አይነቶቹ አንዱን ወይም በተደራቢ የሚሰጥበትን  አማራጭ በመለየት ለኮሚቴው አስተያት ያቀርባል፣


 የኃላፊ ስም፡-   አቶ ገብሩ ገበየሁ


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡-