Search

ኢንፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት


በዚህ የስራ ሂደት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 

በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ያሉ ሶፍትዎሮች፣ ኮምፒተሮችና ተጓዳኝ መሳሪያዎች ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፣ አስፈላጊውን ድጋፍና የጥገና አገልግሎት ይሠጣል፡፡

 

በመስሪያቤቱ የሚገኙትን የኮምፒዩተርና ተጓዳኝ የቢሮ መሳሪያዎችን የጥገና ስራዎችን /computers and office machine Maintenance/ በኃላፊነት ይሰራል፡፡

 

የኔትወርክ አስተዳደር ስራ /Network Administration/ በኃላፊነት ይሰራል፡፡

 

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የውስጥ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ያደራጃል ለተጠቃሚ ተደራሽ ያደርጋል፡፡

 

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተገዝቶ መምጣቱን ያረጋግጣል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ዘመኑን የተከተለ ስፔስፊኬሽን ያወጣል ፡፡

 

መ/ቤቱን የሚመለከቱ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ሥራዎችን ይመራል፡፡

 

ዳይሬክቶሬቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ፕሮጀክቶችን የመቅረጽና ሀብት የማፈላለግ ሥራ ያከናወናል፡፡

 

በመ/ቤቱ የሚከናወኑ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ የሚያመለክቱ መረጃዎችን በዳታቤዝ እንዲለማ የማድረግና ተደረሽነታቸውን የማረጋገጥ ሥራዎችን ያከናወናል፡፡

 

በአሰራር ለመፍታት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ በዘርፉ የሚታዩ እና በተግባር የሚገለጹ የኪራይ ሰብሳቢነትን ምንጭ በማምከን ረገድ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ማዘመንና በግልጽነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድገር ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

 

በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያግዘው  መረጃና የፕሮጀክቶች ሂደት እና አፈጻጸም የመረጃ ቋት ማደራጃ ደንብ፣ መመሪያ እና ማንዋል በማዘጋጀት እና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

 

በመ/ቤቱ የሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶች በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ (e-service) የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

 

የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን የሥራ መሣሪያ በማድረግ ከክልሎችና ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የመረጃ ቅብብሎሹ የተሳለጠ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

 

የመረጃ አያያዝና ቅብብሎሽ አፈጻጸምን በሚመለከት ለክልሎች፣ ለዳይሬክቶሬቶችና  ለፈጻሚዎች ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

 

የመ/ቤቱን የመረጃ ቅብብሎሽ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን የዕድገት አቅጣጫና የተጠቃሚውን ፍላጎት እየተከታተለ ጥናቶች እንዲጠኑና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡


 የኃላፊ ስም፡-  ወ/ሮ ፋንታዬ ኩምሳ


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-15-65-30