Search


የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪና ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች ዐቃቤ


ሕግ ዳይሬክቶሬትአደረጃጀት


ዚህ ዳይሬክቶሬት አራት ማስተባበሪያዎች የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-


የሽብርተኝነትና ተያያዥ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣


የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣ እና


ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች ማስተባበሪያ


በወንጀል የተገኘ ንብረትን ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባበሪያ ናቸው፡፡


በሥራ ክፍሉ ስር ክትትል የሚደረግባቸው ወንጀሎች ምንነት /ባሕርይ/

በዚህ የሥራ ክፍል ስር ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮች በዋናነት በቡድን የሚፈፀሙ፣ ሁሌም ባይሆን አብዛኛውን ጊዜ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ እንዲሁም በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ የሆኑ ናቸው፡፡የተደራጁ ወንጀሎች ሲባል በተለያዩ ምክንያቶች ወንጀል ለመፈፀም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ተሰባስበው አንድ ላይ በመሆን ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ያለውን ሁኔታ የሚመለከት ነው፡፡


ድንበር ተሻጋሪ ባህሪ ያለው ወንጀል የሚባለው ደግሞ  ወንጀሉ በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ እና በሌላ አገር የተፈፀመ እንደሆነ፣ በኢትዮጵያ  የግዛት ክልል ውስጥ ብቻ ወንጀሉ የተፈፀመ ቢሆንም ወንጀሉን ለመፈፀም የተደረገው ዝግጅት፣ ዕቅድ፣ አመራር ወይም የገንዘብ ምንጭ በሌላ አገር የሆነ እንደሆነ፣ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በሌላ አገር ቢሆንም ወንጀሉን ለመፈፀም የተደረገው ዝግጅት፣ ዕቅድ፣ አመራር ወይም የገንዘብ ምንጭ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ እንደሆነ፣ ወንጀሉ የተፈፀመው ከአንድ በላይ በሆኑ አገራት በሚንቀሳቀስ የተደራጀ የወንጀል ቡድን የሆነ እንደሆነ ወይም ወንጀሉ በአንድ አገር የግዛት ክልል ብቻ የተፈፀመ ቢሆንም የወንጀሉ ውጤት በሌላ አገር ወይም በኢትዮጵያ ላይ የደረሰ እንደሆነ ነው፡፡ 


በሌላ በኩል አንዳንድ ወንጀሎች በተደራጀ ቡድን ባይፈፀሙም ወይም የድንበር ተሻጋሪነት ባህሪ ባይኖራቸውም የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ የሆኑና ሀገራዊ እንድምታ ያላቸው በመሆኑ ከዚህ ባህሪያቸው በመነጨ  ይህ የሥራ ክፍል የሚይዛቸውና ክትትል የሚያደርግባቸው ይሆናሉ፡፡


ከዚህ በላይ የተቀመጠው አጠቃላይ የሆነው በሥራ ክፍሉ ስር የሚታዩ ጉዳዮችን ለመለየት የተቀመጠው መስፈርትና የጉዳዮቹ አጠቃላይ የሆነ ባህሪ እንደ መነሻ ተወስዶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወንጀሎች በክፍሉ ስር ክትትል የሚደረግባቸው የወንጀል ዓይነቶች ናቸው ተብለው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡


በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ እና በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ላይ የሽብር ወንጀሎች ተብለው የተዘረዘሩ ወንጀሎች፣


በሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱና በመንግስት የሀገር ውስጥ ደህንነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች /የወንጀል ሕግ አንቀጽ 238-245/፣


በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (Money Laundering) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት (Financing of Terrorism)  ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (አዋጅ ቁጥር 780/2005 )፣


የምርጫ አዋጁን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፤


በመንግስት የውጭ ደህንነት እና በመከላከያ ኃይል ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 246-252)- በዚህ ውስጥ በአገር ነጻነት ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የአገር መከላከያ ኃይልን መጉዳት፣ ክዳትና የኢኮኖሚ ክዳት፣ ከጠላት ጋር መተባበር እና ስለላ ይገኙበታል፤


በውጭ አገር መንግስታት ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 261-266) በባለሥጣኖችና  ዲኘሎማቶች የሚፈፀሙ ግድያዎች እና ሌሎች ወንጀሎችን ጨምሮ፤


ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 269-283) - በዚህ ውስጥ ዘር ማጥፋት፣ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ የጦርነት ወንጀሎች ወ.ዘ.ተ. ይገኙበታል፡፡


በኮምቲውተርና በኢንተርኔት የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 706-710)፤


የሕዝብ ሁከት የሚያነሳሱ ወይም ሊያነሳሱ የሚችሉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 482-488)፤


በማጓጓዣዎችና በመገናኛዎች ነጻነትና ፀጥታ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 505-511)፤


በፖለቲካ ምክንያት ሰውን ማገት ወይንም መጥለፍ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 595)፤


ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር ማሻገር ወንጀል


የህገወጥ መድሀኒቶች እና እጾች ዝውውር ወንጀል


በጦር መሳሪያ መነገድ /ማዘዋወር/የተከለከለ ጦር መሣሪያ መያዝ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 481፣…)፣


በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ወይም ክልሎች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ከባንክ ስራ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (በአዋጅ ቁጥር 592/2000 የተመለከቱት)፤


የቴሌኮም ማጭበርበር  ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (አዋጅ ቁጥር 761/2004)፣


የሚዲያና ፕሬስ ነክ ወንጀሎች፣


በዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤ ናቸው፡፡


የሥራ ክፍሉ አደረጃጀትና የወንጀል ጉዳዮቹ ክትትል የሚደረግባቸው ደረጃ


ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የወንጀል ጉዳዮች በተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ የወንጀል ጉዳዮችን በሚከታተለው ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የሚያዙ ሲሆኑ የሥራ ክፍሉ በአስሩ የክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምድብ ጽ/ቤቶች እና በድሬዳዋቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት አደረጃጀቱን በማውረድ ሥራዎቹን ያከናውናል፡፡የወንጀል ጉዳዮችን ክትትል በየደረጃው ለመመደብ የተለያዩ መመዘኛዎች ታሳቢ የሆኑ ሲሆን እንደአጠቃላይ  የወንጀሎቹ አፈፃፀም ክብደት እና ውስብስብነት፣ ወንጀሎቹ በአገር አቀፍ ደረጃ እና ከአገር ውጭ ሊኖራቸው የሚችለው ተያያዥነት፣ በተቻለ መጠን አገልግሎቶቹ ለዜጎች ተደራሽ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መሰጠት የሚገባቸው መሆኑ ግምት ውስጥ መግባት የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡  


ከዚህ ባሻገር በሕግ በግልጽ የተወሰኑ የወንጀል ጉዳዮች በአንድ ቡድን (ቦታ) አማካኝነት ተይዘው ክትትል እንዲደረግ በተደነገገበት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 በአንቀጽ 28 (2) መሠረት አደረጃጀቱ ይህን የተለየ ሁኔታም ታሳቢ በማድረግ እንዲሰራ ሆኗል፡፡


በሥራ ክፍሉ በራሱ በማዕከል ደረጃ የሚታዩትን/ክትትል የሚደረግባቸውን/ የወንጀል ጉዳዮች


በተለያየ ደረጃ መታየት የሚኖርባቸውን የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተመለከተ በመለያ መስፈርትነት ሊቀመጥ የሚገባው መመዘኛ በዋናነት ወንጀሎቹ የሚያስከትሉት የቅጣት መጠን ሆኖ በሚያስከትሉት የቅጣት መጠን በታችኛው የመከታተያ አካል ሊታዩ የሚችሉ ቢሆኑም በሌሎች የተለዩ ምክንያቶች በቀጥታ በሥራ ክፍሉ ሊያዙ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል፡፡


እነዚህም የተለዩ ምክንያቶች በህብረተሰቡ ውስጥ የፈጠሩት ስሜትና ጉዳዩ የሚያስከትለው የፖለቲካ እንድምታ፣ ተከሳሹ የነበረው የሥልጣን ደረጃ የመሳሰሉት ናቸው፤


በዚህም መሠረት በተወሰኑ እና በተመረጡ የወንጀል ዓይነቶች ማለትም ተከሣሹ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን በሚሆንበት ጊዜ፣ ወንጀሉ በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ወይም ክልሎች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ወንጀሉ በህብረተሰቡ ውስጥ የፈጠረው ስሜትና ጉዳዩ የሚያስከትለው የፖለቲካ እንድምታ ከፍተኛ ከሆነ በሥራ ክፍሉ በራሱ አማካኝነት ጉዳዩ ክትትል የሚደረግበት ይሆናል፡፡


ስለዚህ ከለይ የተቀመጡ መስፈርቶችን ከግምት በማስገባት ከዚህ ታች የተዘረዘሩ ጉዳዮች በዳይሬክቶረት ደረጃ የሚታይ ይሂናል፡፡


በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ እና በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ላይ የሽብር ወንጀሎች ተብለው የተዘረዘሩ ወንጀሎች፣


በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (Money Laundering) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት (Financing of Terrorism)  ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (አዋጅ ቁጥር 780/2005 እንዲሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 684)


የኮምፒዩተር ወንጀሎች፣


ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 269-283) - በዚህ ውስጥ ዘር ማጥፋት፣ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ የጦርነት ወንጀሎች ወ.ዘ.ተ. ይገኙበታል፡፡


ከባድ የሆኑ በጦር መሳሪያ መነገድ /ማዘዋወር/ የተከለከለ ጦር መሣሪያ መያዝ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 481፣…) ፣ (ለምሳሌ ከሚዘዋወሩ መሳሪያዎች ብዛት እና መሳሪያው በእጃቸው እንዲገባ ከተደረጉ ሰዎች አደገኛነት አንጻር) በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ወይም ክልሎች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ፍጻሜ ያገኙ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በወንጀል ህጉ አንቀጽ 525/1/፣ /2/ሀ/ ስር የሚወድቁ የአደገኛ ዕጽ ዝውውር በፖለቲካ ምክንያት ሰውን ማገት ወይንም መጥለፍ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 595)፤


በውጭ አገር መንግስታት ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 261-266) በባለሥጣኖችና ዲኘሎማቶች የሚፈፀሙ ግድያዎች እና ሌሎች ወንጀሎችን ጨምሮ፣


በመንግስት የውጭ ደህንነት እና በመከላከያ ኃይል ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 246-252)- በዚህ ውስጥ በአገር ነጻነት ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የአገር መከላከያ ኃይልን መጉዳት፣ ክዳትና የኢኮኖሚ ክዳት፣ ከጠላት ጋር መተባበር እና ስለላ ይገኙበታል፣


በሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱና በመንግስት የሀገር ውስጥ ደህንነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች /የወንጀል ሕግ አንቀጽ 238-245/፣

ሀገራዊ አንድምታ ያላቸው የምርጫ አዋጁን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ (ለምሳሌ በተለያዩ ሚዲያዎች የምርጫ ውጤትን ከመተንበይ ጋር የተያያዙ)፣


በማጓጓዣዎችና በመገናኛዎች ነጻነትና ፀጥታ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 505-511)፣


ከባንክ ስራ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በአዋጅ ቁጥር 592/2000 የተመለከቱት እና

ከቴሌኮም ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 761/2004፣


በዋና ዋና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤


የሚዲያ እና ፕሬስ ነክ ወንጀሎች፣


ከላይ በተዘረዘሩ ወንጀሎች አማካኝነት ህገወጥ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀሎች ናቸው፤


የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ እና ሀገራዊ ጉዳትን የሚያስከትሉ ወንጀሎችን በተመለከተ በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ/ቤቶችደረጃክትትልየሚደረግባቸውየወንጀልጉዳዮች፣


የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና ሀገራዊ ጉዳትን የሚያስከትሉ በሚል ከተለዩት ወንጀሎች በምድብ ጽ/ቤቶች የሚታዩ የሚሆኑት፡-


በምርመራ ሂደታቸው ውስብስብ ያልሆኑ፣


በወቅታዊነታቸው በአንድ ማዕከል መያዛቸው አስፈላጊ የማይሆኑ፣


በጽ/ቤቶች ስልጣን ስር ከሚወድቁ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ህጋዊ ያልሆነ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀሎች፣ እና በግልጽ ዳይሬክቶሬቱ በራሱ ክትትል እንዲያደርግባቸው ያልተሰጡ የወንጀል ጉዳዮች በምድብ ጽ/ቤቶች የሚታዩ ይሆናሉ፡፡ 


በተደራጁ፣ድንበር ተሻጋሪ እናሀገራዊጉዳትየሚያስከትሉ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት  ስር የተደራጁ ማስተባበሪያዎች የሚከታተሏቸው ጉዳዮች ዝርዝር


በስራ ሂደቱ በተደራጁ ማስተባበሪያዎች ስር ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮች፡-


በሽብርተኝነትና ተያያዥ ወንጀሎች ጉዳዮች ማስተባበሪያ-


በዚህ ማስተባበሪያ ስር ክትትል የሚደረግባቸው የወንጀል ጉዳዮች፡-


በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ እና በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2009 ላይ የሽብር ወንጀሎች ተብለው የተዘረዘሩ ወንጀሎች፣


በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (Money Laundering) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት (Financing of Terrorism)  ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (አዋጅ ቁጥር 780/2005 እንዲሁም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 684)


በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ከሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች ጋር ተያይዞ ሊታይ እና ምርመራና ክስ ሊቀርብ የሚችል ጉዳይ ቢሆንም በዋናነት በወንጀሉ ጉዳይ ላይ የሚሰራው ግን ይህ ማስተባበሪያ ይሆናል፡፡በመሆኑም ሌሎች ከሚከታተሏቸው ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ሊቀርቡ የሚገቡ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ የማቅረብ የወንጀል ጉዳዮችን ይህ ምደባ አይከለክልም፣ እና የኮምፒዩተር ወንጀሎች፣


የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ማስተባበሪያ -


በዚህ ማስተባበሪያ ስር ክትትል የሚደረግባቸው የወንጀል ጉዳዮች፡-


ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 269-283) - በዚህ ውስጥ ዘር ማጥፋት፣ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ የጦርነት ወንጀሎች ወ.ዘ.ተ. ይገኙበታል፡፡


በጦር መሳሪያ መነገድ /ማዘዋወር/የተከለከለ ጦር መሣሪያ መያዝ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 481፣…) በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ወይም ክልሎች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


በፖለቲካ ምክንያት ሰውን ማገት ወይንም መጥለፍ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 595)፤


በውጭ አገር መንግስታት ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 261-266) በባለሥጣኖችና  ዲኘሎማቶች የሚፈፀሙ ግድያዎች እና ሌሎች ወንጀሎችን ጨምሮ፣


በመንግስት የውጭ ደህንነት እና በመከላከያ ኃይል ላይ የሚደረጉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 246-252)- በዚህ ውስጥ በአገር ነጻነት ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የአገር መከላከያ ኃይልን መጉዳት፣ ክዳትና የኢኮኖሚ ክዳት፣ ከጠላት ጋር መተባበር እና ስለላ ይገኙበታል፣


በጦር መሳሪያ መነገድ /ማዘዋወር/የተከለከለ ጦር መሣሪያ መያዝ (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 481፣…) የአደገኛ ዕጽ ዝውውር፣

የህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሚዲያ እና ፕሬስ ነክ ወንጀሎች፣


ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች ማስተባበሪያ -


በዚህ ቡድን ማስተባበሪያ ክትትል የሚደረግባቸው የወንጀል ጉዳዮች፡-


በሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱና በመንግስት የሀገር ውስጥ ደህንነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች /የወንጀል ሕግ አንቀጽ /238-245/፣


የምርጫ አዋጁን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣


የሕዝብ ሁከት የሚያነሳሱ ወይም ሊያነሳሱ የሚችሉ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 482-488)፣


በማጓጓዣዎችና በመገናኛዎች ነጻነትና ፀጥታ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 505-511)፣


ከባንክ ስራ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በአዋጅ ቁጥር 592/2000 የተመለከቱት፣


ከቴሌኮም ማጭበርበር ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች አዋጅቁጥር 761/2004፣


በመሠረተ ልማተ አውታሮች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ወንጀል የተገኙ ንብረቶች ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባቢያ

በዚህ ቡድን ማስተባበሪያ ክትትል የሚደረግባቸው የጉዳዮች-

ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች ለወንጀሉ መፈፀሚያ የዋሉ ንብረቶችን ወይም ከወንጀሉ ፍሬ ሆነው የተገኙ ንብሬችን በመከታተከል እና በመለየት በህጉ መሰረት እንዲከበር እንዲወረስ እና በወንጀሉ ምክንያት የጠፋ ሃብት ወይም የደረሰ ጉዳት ካለ እንዲካስ የማድረግ ሃላፊነትን የሚወጣ ቡድን ይሆናል፡፡


    የኃላፊ ስም፡-  አቶ ፍቃዱ ጸጋ


    የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-34-31