Search

የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ጽቤት


በዚህ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 

በአገር አቀፍ ደረጃ የድርጊት መርሐ ግብሩን አፈጻጸም በቴክኒክ ደረጃ በዚህ መርሐ ግብር በተሰጡት ኃላፊነቶች እና በብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጡት አቅጣጫዎች መሰረት ይከታተላል።

 

በመርሐ ግብሩ እንዲከናወኑ የተቀመጡ ተግባራት፤ ፈጻሚ አካላት ተብለው በተለዩት የፌዴራል፣ የክልል እና ከተማ መስተዳድር ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ መካተታቸውን ይከታተላል፤

 

በየክልሉና ከተማ መስተዳድሮች የፍትህ ቢሮዎች ውስጥ ከተደራጁት የድርጊት መርሐ ግብሩ ጽ/ቤቶች ጋር በቅርበት ይሰራል።ጽ/ቤቶቹ የግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በወቅቱ አሰባስበው መላካቸውን ይከታተላል፤

 

የግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ አገር አቀፍ የድርጊት መርሐ ግብሩን አፈጻጸም ሪፖርት በማጠናቀር ለብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ያቀርባል፤ 

 

በዓመት አንድ ጊዜ አገር ዓቀፍ የፖሊስ፣ ሚሊሻ እና ማረሚያ ቤቶች ተቋማት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርት በማጠናቀር ለብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ያቀርባል፤

 

በኮሚቴው በሚሰጡት አቅጣጫዎች መሰረት ሁሉም ፈጻሚ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የሚገኙበት የመገማገሚያ መድረኮችን ያደራጃል፤

 

የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነት ማስፈጸሚያ አደረጃጀቶች ለሃገራችን የሚሰጧቸው ምክረ ሃሳቦች እና ግብረ መልሶች የሚፈጸሙበትን ሁኔታ ይከታተላል፤

 

የድርጊት መርሐ ግብሩ የማስፈጸሚያ ጊዜ ሲያበቃም መርሐ ግብሩ ግቡን መምታቱን ለማረጋገጥ አጠቃላይ ምዘና የሚካድበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

 

ቀጣይ የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር የሚዘጋጅበትን ሁኔታ ከብሔራዊ  አስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያስተባብራል።

 

በስሩ በሚኖረው የተለየ ቡድን አማካኝነት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን እንደአንድ የመንግስት ተቋም በመውሰድ በሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሀ ግብር የተሰጡትን ሃላፊነቶች አፈጻጸም ይከታተላል፣ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አማካኘነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል እና ተፈጥመውም ሲገኙ ተገቢውን የማስተካከያ ርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ስራዎችን ይሰራል ወይም አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፡፡ 

 

 የኃላፊ ስም፡-   አቶ ይበቃል ግዛው


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-54-35-92