Search

የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


በዚህ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 

የሴቶች፣ ህፃናት ወጣቶች እና ባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን ለማካተት የሚያስችል የማካተቻ  መመሪያ (Guideline) ማዘጋጀት፣

 

በተዘጋጀው የማካተቻ መመሪያ መሰረት በእቅድ ውስጥ መካተቱን እና መፈፀሙን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቼክሊስት ማዘጋጀት፣

 

የሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶችና ሌሎች የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች አገልግሎት አፈፃፀምና አካቶ ከመፈፀም አንጻር ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣ እንዲሁም ግብረ-መልስ መስጠት፣

 

ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ላይ የስልጠና እና የግንዛቤ ማደበሪያ ስራዎች ለፈፃሚዎች፣ አመራሮችና ለማህበረሰብ መስጠት፡፡ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ባዘጋጇቸው መድረኮች ላይ በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠት፣

 

በጽ/ቤቶች ከሴቶችና ህፃናት ምርመራ ቡድን እና የፍትሐብሔር ዳይሬክቶሬት፣ መርመርና ወሳኔ ማሰጠት ዳይሬክቶሬትና ጥብቅና ፈቃድ አስተዳደር ዳይሬክቶሬትና ሌሎች ከሚመለከታቸው የውስጥ የሥራ ሂደቶች ጋር በየወሩ የዉይይት እና የተሞክሮ ልዉዉጥ መድረክ ማዘጋጀት፣

 

ከሴቶችና ህፃናት ምርመራ ቡድን ጋር በመሆን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ የማህበረሰብ የግንዛቤ መፍጠሪያና የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን፣

 

በተቋሙ የሚሰሩ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው የሚገኙ ሠራተኞች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸው እንዲጎለብት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራት እና በተቋሙ እነሱን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች እንዲቀረፁ ማድረግ፣

 

በተቋሙ የሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው የሚገኙ ሠራተኞች በህግ የተረጋገጡ መብቶችን ማስፈፀም የሚያስችሉ አደረጃጀቶች መቀረፃቸውን መከታተል፣ የተፈጠሩ አደረጃጀቶች መብቶቻቸውን ማስፈፀም የሚያስችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥና መከታተል፡፡

 

በተቋሙ የሚቀረፁ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው የሚገኙ ሰዎችን እና ሌሎች የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አካተው መቀረፃቸውን መከታተል፣ ማረጋገጥና ድጋፍ ማድረግ፣

 

የስርዓተ ጾታ ጉዳዮች በተቋሙ መካተታቸውን መከታተል፤ የሴቶች ተሳትፎና አመራርነትን ደረጃ ለማሳደግ ድጋፍ ማድረግ

 

ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋዉያን፣ አካል ጉዳተኛ ሠዎች እና ሌሎች ባለብዙ ዘርፈ ጉዳዮች የተመለከተ ብሮሸር፣ በበራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና ቢልቦርድ ማዘጋጀት እንዲሁም በሬዲዮ፣ በፕላዝማ እና በቴሌቪዥን በመጠቀም የግንዛቤ ማዳበሪያ ስራዎች፣

 

በሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች አስመልክቶ በወጡ፣ አዲስ በሚወጡት ህጐች እና አሠራሮች ዙሪያ የታዩ ክፍተቶች በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ ወይም እንዲጠና ለህግ ማረቀቅ ማስረፅ ዳይሬክቶሬትና የህግ ጥናት እና ፍትህ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት መነሻ ሃሳብ ማቅረብ፣

 

ለሥራ ሂደቶችና ጽ/ቤቶች አመራርና ፈፃሚዎች ክህሎት ለማደበር እንዲሁም የወንጀል ተጐጂ የሆኑ ሴቶች፣ ህፃናት ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና ምስክሮች የድጋፍ ፍላጐቶችን ለማሟላት የሚያስችል የሀብት ማፈላለግ ፕሮጀክቶች በመቅረጽ፣

 

በተቀናጀ እና ሁሉን አቀፍ በሆነ ሁኔታ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን   ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመውን የብሔራዊ አስተባባሪ አካልና ቴክኒክ ኮሚቴ ቅንጅት ማስተባበር እና አባል ከሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት፣

 

በሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሥነ-ህዝብ፣ ኤች.አይ.ቪ እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ተግባራትን ማከናወን፣

 

ክልሎች በሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከመከላከልና ምላሽ ከመስጠት አንፃር እና የፍትህ አገልግሎት ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር እንዲሁም የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አካተው ለመፈፀም የሚችሉበትን ሁኔታ በተመለከተ የቴክኒክና አቅም ማጎልበት ድጋፍ ማድረግ፣

 

የተቋሙን አመራርና ፈፃሚዎች አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ ስልቶችን በተከተለ መልኩ ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋዉያን፣ አካል ጉዳተኛ ሰዎች እና ሌሎች ባለብዙ ዘርፈ ጉዳዮች የተመለከቱ ዓለም አቀፍ በዓላትን ማክበር፣

 

ተቋሙን በመወከል የሴቶች፣ ህፃናት ወጣቶች እና ባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮች በተመለከተ ያለንየአፈፃፀም መረጃ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ሌሎች ለሚመለከታቸው ሚኒስቴር መ/ቤቶች እንዲሁም በአለም አቀፍ መድረኮች ማቅረብ፣

 

በሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች ዙሪያ የተጠናቀረ ወቅታዊ እና ግልጽ መረጃ ማደረጃት፣

መረጃና የሥራ አፈፃፀም በማጠናቀር ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ማቅረብና ማሰራጨት፡፡


 የኃላፊ ስም፡-  ወ/ሮ ዕንቁ አስናቀ

 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-53-16-86