Search

  የሰው ኃይል አስተዳደር  ዳይሬክቶሬት 


በዚህ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 

ከሥራ ክፍሎች የሚቀርቡትን የቅጥር፣ የዝውውር እና የደረጃ ዕድገት ጥያቄዎችን ተቀብሎ በተፈለገበት ወቅት እንዲሟላ ያደርጋል፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ሰው ኃይል ፍላጎት ለማርካት በተፈለገው መጠንና ጥራት የተሟላ /የተመደበ/ የሰው ኃይል መኖሩን ማረጋገጥመ/ቤቱ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂካዊና ዓመታዊ ዕቅዶችንና ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል በዕውቀታቸው፣ በክህሎታቸውና በአመለካከታቸው የዳበሩ ባለሙያዎችን ያሟላል፤

 

በየሥራ ሂደቱ የሠራተኞች የውጤት ተኮር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሞላላቸውና የተሞላላቸውም ውጤት በአግባቡ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፡፡ የሥራ አፈጻጸም ሥራ አመራር (Performance Management) ሥርዓት በመ/ቤቱ እንዲዘረጋ ያደርጋል፤

 

የመ/ቤቱን የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን ሠራተኞች በሥልጠና በመደገፍና ክህሎታቸውን በማሳደግ ለሥራ ዝግጁ ያደርጋል

 

የመ/ቤቱ ሠራተኞች ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ለሠራተኞች ተስማሚና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር በሥራ አካባቢ የሚኖሩ ችግሮችን በመዳሰስ የመፍትሔ እርምጃ በማቅረብና በማስወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፤

 

የመስሪያ ቤቱን የሰው ሀብት ፍላጎት በማጥናት አማራጭ የአደረጃጀት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ተግባራዊ ያደርጋል፤

 

የተደራጀ የሰው ሀብት መረጃ እንዲኖርና ወቅታዊና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፤

 

በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ እና በየጊዜው የተላለፉ የአፈጻጸም መመሪያዎች ሕጎች በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፤ የሠራተኞች መብቶች መጠበቃቸውንና ሠራተኞችም ተገቢውን የሥራ ዲሲፕሊን ማክበራቸውን እያረጋገጠ ለሚነሱ ቅሬታዎች፣አቤቱታዎችና ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፤

 

ሠራተኞች የሚፈልጓቸውን የግልና የሥራ ሁኔታ ማስረጃዎችን/መግለጫዎችን በመስጠትና ሌሎች የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎች ላይ ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት ፍላጎታቸውን ያሟላል፤

 

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ  ውስጥ የሚኖረውን የአስተዳደርና ፋይናንስ የሰው ሃይል ፍላጎት ጥናት በማካሄድ በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ስልት ይቀይሳል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ  በአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ የሚመደብ የሰው ኃይል ለምድቡ የተሟላ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው እንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

 

የአገር ውስጥ ባለሙያዎች በአካባቢው አገሮችና በአለም አቀፍ ደረጃ በሙያቸው ሊሳተፉና ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

 

በአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን መረጃ ይይዛል፤

 

ዳይሬክቶሬቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ሀብት የማፈላለግ ሥራ ያከናወናል፤

 

የባለሙያዎችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር ስርዓት እንዲኖርና እንዳስፈላጊነቱ እንዲከለስ ያደርጋል፤

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሰው ሀይል አስተዳደር በየትኛውም ደረጃ የሚመደብ የሰው ኃይል ለምድቡ የተሟላ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው መሆኑን በማጥናት ክፍተት ይለያል፤

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ እንዲሁም የስራ ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤


በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከምዘና ማዕከላት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የባለሙያዎችን ምዘና እንዲካሄድ ያደርጋል፤

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሚሰጠው ምዘና ብቁ ያልሆኑትን ባለሙያዎች ተጨማሪ ስልጠና እንዲያገኙ እና በድጋሚ እንዲመዘኑ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

 

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የማነቃቂያ ሥልጠና እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

 

ከትምህርት ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለዘርፉ የሚያስፈልጉ የሙያ ዓይነቶችበካሪኩለም ውስጥ የሚካተቱ በፍትህ ዘርፍ የተሰማሩና የአቅም ግንባታ የተፈጠረላቸው ባለሙያዎችን መረጃ ይይዛል፤

 

ዳይሬክቶሬቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ የፕሮጀክት መነሻ ሀሳቦችን ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን በመከታተል ያስፈጽማል፤


 የኃላፊ ስም፡-  ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ማሪያም


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-58-03-62