Search

የሙስና ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት


አደረጃጀት

በዚህ ዳይሬክቶሬት ስር 4 ማስተባሪያዎች የተደራጁ ሲሆን እነኚህም፡-

 1. በአሰራር ላይ የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች ማስተባሪያ
 2. ተገቢ ያልሆነ ጥቅም በመቀበልና በመስጠት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ማስተባበሪያ 
 3. ሀሰተኛ ሰነድ በመፍጠርና በማታለል የሚፈፀመውን የሙስና ወንጀል ማስተባበሪያ እና
 4. በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባበሪያ ናቸው፡፡

በሥራ ክፍሉ ስር ክትትል የሚደረግባቸው ወንጀሎች ምንነት /ባሕርይ/

የሙስና ወንጀሎች ምንነት በወንጀል ህጉ ከተደነገገ ውጪ በተለየ አዋጆች ተደንግጎ ሲሰራበት እንደነበር የሚታወቅ ሆኖ ሌሎች ወንጀሎች ማካተት ስለነበረበት የግል ዘርፍ አካላት የሚፈፅሙት የጉበኝነት ምዝበራ እና ተመሳሳይ ወንጀሎችን አንድ ላይ በማጣመር በአዋጅ ቁጥር 881/ 882/ 883/07 ዓ.ም ተቋቁሞ እና በወንጀል ህግ ተደንግጎ ተግባር ላይ ውሏል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሙስና ወንጀል ባህሪያቸውን በፈጣን ሁኔታና በተለያየ መንገድ እየተቀያየሩ የሚፈፅሙ ቢሆንም በሚፈፀመው ወንጀልና ከአፈፃፀማቸው ጋር ተያያዥነት ያለው ማስረጃዎችን በመመዘን ጉዳዩን ለሚያየው ፍ/ቤት ቀርበው ተገቢውን ውሳኔ ማግኘታቸው ተገቢ ቢሆንም በዚሁ የሥራ ክፍል አደረጃጀት ተዋረድ ውስጥ የትኞቹ የሙስና ወንጀሎች መታየት አለባቸው ለሚለው እንደሚከተለው ተመላክተዋል፡፡

ሙስና ወንጀል ጉዳዮች የሥራ ክፍል በየደረጃው መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ለመለየት በዋና መመዘኛነት የተቀመጡ የመለያ መስፈርቶች፡-

በባለ ስልጣናት ማለትም በፓርላማ የተሾሙ፣ ሚኒስትሮች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም በክልል ምክር ቤት የተሾሙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሆነው  የፈፀሙት የሙስና ወንጀሎች በፌዴራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ በሚሆንበት ጊዜ፤

የወንጀሎቹ ውስብስብነት እና ከባድነት በመመዘኛነት ተወስዷል፤

በዚህመ መሰረት፡-

በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት/በማዕከል/ የሚታዩ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች በመርህ ደረጃ፡-

 • ከአስር ዓመት ፅኑ እስራት በላይ የሚያስቀጡ የሙስና ወንጀሎች፣


 • በአሰራር ላይ የሚፈፀሙ በስልጣን ያለ አግባብ መገልገልና የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት (ሆኖም በንዑስ አንቀጽ 1 ስር የሚወድቁት በምድብ ደረጃ ክትትል የሚደረግባቸው ይሆናል)፣


 • በተደራራቢነት የተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ሆነው ዋስትናን የሚያስከለክሉ ሲሆኑ፣


 • ሙያዊ እና የፎረንሲክ ምርመራን የሚሹ የሙስና ወንጀሎች፣


 • ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀል፣


የሙስና ወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ  በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት ደረጃየሚታ የሙስና ወንጀሎች በመርህ ደረጃ፡-


 • ከአስር ዓመት እስራት በታች  የሚያስቀጡ የሙስና ወንጀሎች፣


 • በአሰራር ላይ የሚፈፀሙ በስልጣን ያለ አግባብ መገልገልና የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት በንዑስ አንቀጽ 1 ስር የሚወድቁ ከሆኑ፣


 • ከእነዚህ የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀል፣


 • በአጠቃላይ በማዕከል ደረጃ ከሚታዩት ከላይ ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉ ሌሎች የሙስና ወንጀሎች በተቀመጠው ጠቅላላ መርህ መሰረት በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጽ/ቤቶች ደረጃ የሚታዩ ይሆናል፡፡


በሙስና ዳይሬክቶሬት  ስር የተደራጁ ማስተባበሪያዎችየሚከታተሏቸው ጉዳዮች ዝርዝር

በአሰራር ላይ ሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣ 


 • በስልጣን አለአግባብ መገልገል፣ 


 • የመንግስት ወይም ህዝባዊ ድርጅቶች ስራን በማይመች አኳሃን መምራት፣


 • አደራ የተሰጠው እቃ ያለ አግባ ማዘዝ፣


 • በስራ ተግባር የሚፈፀሙ የመውሰድና የመሰወር ወንጀል፣


 • በስልጣን ወይም በሃላፊነት መንገድ፣


 • ያለ አግባብ ጉዳይን ማጓተት፣ 


 • ያለ አግባብ ፈቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ፣


 • የስራ ሚስጥርን መግለፅ፣


 • በሌላው ስልጣን መጠቀም፣


 • በግል ተስማሚነት መነገድ፣


ተገቢ ያልሆነ ጥቅም በመቀበልና በመስጠት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣ 

 • ጉቦ መቀበል፣


 • የማይገባ ጥቅምን መቀበል፣


 • አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች የሚፈፅሙት ጉቦ መቀበል ወንጀል፣


 • በሙስና ወንጀሎች  የተገኘ በገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ስለመረዳት፣


 • በህገ ወጥ መንገድ ያለውን ነገር ያለ ክፍያ ወይም በቂ ክፍያ ማግኘት፣


 • ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ይዞ መገኘት፣


 • ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት፣ 


 • ዋጋ ያለው ነገር ያለ በቂ ክፍያ መስጠት፣


 • ገንዘብ ማቀባበል፣


 • በምርጫ ላይ ሚስጥር መደለያ፣


ሀሰተኛ ሰነድ በመፍጠርና በማታለል የሚፈፀመውን የሙስና ወንጀል ማስተባበሪያ፣ 


 • የመንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነድ ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ፣


 • በከባድ አታላይነት የሚፈፀመው የሙስና ወንጀሎች፣


 • በከባድ እምነት ማጉደል የሚፈፀመው የሙስና ወንጀሎች፣

 • መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል፣


በወንጀል የተገኙ ንብረቶች ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ቡድን

ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች ለወንጀሉ መፈተሚያ የዋሉ ንብረቶችን ወይም ከወንጀሉ ፍሬ ሆነው የተገኙ ንብሬችን በመከታተከል እና በመለየት በህጉ መሰረት እንዲከበር እንዲወረስ እና በወንጀሉ ምክንያት የጠፋ ሃብት ወይም የደረሰ ጉዳት ካለ እንዲካስ የማድረግ ሃላፊነትን የሚወጣ ቡድን ይሆናል፡፡

የኃላፊ ስም፡-  አቶ ተረፈ አሰፋ

የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-34-99