Search

የሕግ ኦዲት፣ ቅሬታ ማስተናገጃና የስነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት


ይህ የስራ ክፍል በተቋሙ የሚከናወኑ ስራዎች ህግን ተከትለው እየተፈጸሙ መሆኑን መከታተል፤ ተገልጋዮች የሚያቀርቡትን ቅሬታዎች በማጣራት የውሳኔ ሐሳብ ለበላይ አመራሮች ማቅረብ እና ዐቃብንያነ ሕግና ሌሎች ሰራተኞች የሞያ ስነምግባራቸውን ጠብቀው ስራቸውን መከናወናቸውን ክትትል የሚያደርግ የሥራ ክፍል ነው፡፡ በውስጡምየሕግ ኦዲት፣ የዜጎች አገልግሎትና ቅሬታ ማስተናገጃና የስነ ምግባር መከታተያማስተባበሪያዎች ተደራጅተዋል፡፡

ተግባርና ኃላፊነቶቹም፡-


የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 42(1)(ሀ)ን ጨምሮ  በተለያየ መንገድ በምርመራ መዝገብ ላይ የተሰጡ የማቋረጥ ወይም የመዝጋት ዉሳኔዎችን ሕጋዊነትና አግባብነት መመርመር፣


ለፍ/ቤት የቀረቡ ክሶች በሕግ አግባብ የቀረቡ መሆኑን በታቀደ ወይም ድንገተኛ  የሕግ ኦዲት ሥራ ማረጋገጥ


ጥቆማን ወይም የበላይ አመራር ትዕዛዝን መነሻ በማድረግ ማንኛዉንም የዐቃቤ ሕግ ዉሳኔዎችን ሕጋዊነት  በኦዲትና ኢንስፔክሽን ማረጋገጥ፣


በችሎት የሚደረጉ ክርክሮችን አግባብነት በአካል በሚከናወን የኢንስፔክሽን ሥራ ማረጋገጥ፣


ዐቃቢያነ ሕግ በተቋሙ የወጡ መመሪያዎችንና የተዘረጉ አሰራሮችን ጠብቀዉ እየሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ፡


በኦዲት ግኝቶች ላይ ተመስርቶ ግብረ መልስና ማስተካከያ እንዲደረግ ለኦዲት ተደራጊዉ የሥራ ክፍል መላክና የበላይ አመራሩ እንዲያዉቀዉ ማድረግ


የኦዲት ግኝትን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን የእርምት እርማጃ እንዲወሰድ ማድረግ እና


በኦዲት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ሌሎች የሥራ ክፍሎች እንዲማሩበት ማድረግና  ከሚመለከታቸዉ ክፍሎች ጋር በመተባበር ምርጥ ተሞክሮዎችን በስልጠና ጭምር የማስፋት ሥራ መስራት


ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል አጣርቶ ለበላይ አመራር የዉሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣


በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚቀርቡ ማንኛዉንም ቅሬታዎች ተቀብሎ በሚመለከተዉ ክፍል እንዲጣሩ ወይም እንዲፈቱ መላክ


ከበላይ አመራሩ የሚመሩ ቅሬታዎችን አጣርቶ የዉሳኔ ሀሳብ ማቅረብን የሚያካትት ሲሆን፤


በሚመለከታቸዉ ክፍል እንዲጣሩና መፍትሔ እንዲሰጣቸዉ በዳይሬክቶሬቱ የተላኩ አቤቱታዎች/ቅሬታዎች በወቅቱ ምላሽ ስለማግኘታቸዉ መከታተል፣


ተገልጋዮች በዜጎች ቻርተር መሰረት አገልግሎት እያገኙ መሆን አለመሆኑንና መከታተልና በተቋሙ ያለዉን የተገልጋዮችን የእርካታን ደረጃ በጥናት የመለየት፣


በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አገልግሎት መስጫ የሥራ ቦታዎች ዜጎች አገልግሎት የሚያገኙባቸውን ቢሮዎች የሚያመላክት አቅጣጫ ጠቋሚ ከመግቢያ በር ላይ በግልጽ መቀመጡን ማረጋገጥ፣


በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አገልግሎት መስጫ የስራ ቦታዎች እና ፖሊስ ጣቢያዎች አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች ለሚሰጡት አገልግሎት መቼ እንደሚሰጡና በቢሯቸው በር ላይ ዋና ዋና ተግባራት (የዜጎች ቻርተር) መለጠፋቸውንና የፈፃሚው ስምና ኃላፊነት፣ የጠረጴዛ መለያና የደረት ባጅ ተዘጋጅቶ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን መከታተል፣


በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አገልግሎት መስጫ የስራ ቦታዎች እና የፖሊስ ጣቢያዎች ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ አቤቱታ የሚያቀርቡባቸው ፎርሞች የአስተያየት መስጫ ሳጥንና መዝገብ በግልጽ ቦታ መቀመጡን ማረጋገጥ፣


በተቋሙ በዋና መ/ቤትም ሆነ በምድብ ጽ/ቤት ጠቅላይ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ደረጃ በተዘጋጀው የተገልጋዮችና የዜጐች ቻርተር ስታንዳርድ መሠረት ለተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን መከታተል፣


በተቋሙ ዉስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፣


በፀረ-ሙስና፣በሥራ ዲስፕሊን፣ በሙያ ሥነ-ምግባር፣በሕዝብ አገልጋይነትና ኃላፊነት ስሜት ላይ የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን መሸከም ማይችል ሠራተኛ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ፣


የፀረ-ሙስና ፖሊሲዎችና ሕጎች መከበራቸዉን መከታተል፤ ስለ አፈጻጸማቸዉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉን ማማከር፣


የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር እንዲጋለጥ፣ እንዲመረመርና በአጥፊዎች ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ፣


የሙስና ወንጀል የሚያጋልጡ ሰራተኞች ላይ የቂም በቀል እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የበላይ አመራሩን ማማከር፣


የተቋሙን የሙስና መከላከያ ስትራቴጅ ተግባራዊነት ይከታተላል፣


ተቋማዊ የሙስና መከላከል ካዉንስል ሴክሬታሪያት ሥራዎችን ያከናዉናል፣


ሠፊ የዐቃቢያነ ሕግ ፍቅደ ስልጣን ያለባቸዉን ኃላፊነቶችን ለይቶ መገደብ የሚያስችሉ አመላካቾችን በመለየት ዝርዝር መመሪያ እንዲወጣላቸዉ ማድረግ፣


ዳይሬክቶሬቶችና ምድብ ጽ/ቤቶች በተቀመጠዉ የተቋሙ አሰራርና ሕግ መሰረት አገልግሎት ስለመስጠታቸዉ ማረጋገጥ እና የቅሬታ ምንጮችን በጥናት በመለየት የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣


የሥነ-ምግባር ጥሠቶችን ወይም ጥቆማዎችን ተቀብሎ በማጣራት ለበላይ አመራር የዉሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣


የተቋሙ ሠራተኞች ቅጥር፣ዕድገት፣ዝዉዉር ወይም ስልጠና እንዲሁም ማንኛዉም የግዥ አገልግሎት ከሕግና ደንብ ዉጭ ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ማስተካከያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ማቅረብ፣


ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በጥናት የመለየትና የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣


የሥነ-ምግባር መኮንኖች በየዳይሬክቶሬት ፣ ምድብ ጽ/ቤቶችና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች  የተማሉ መሆኑን በማረጋገጥ መደገፍና ሥራዉን መምራት፣


በተቋሙ በየደረጃዉ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ከተገልጋዮችና ሕብረተሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት፣ነጻ የስልክ ጥሪን እና ሌሎች አማራጮችን መፍጠር እና


ሌሎች በሚንስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 144/2000 የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች መተግበር፣ 


የኃላፊ ስም፡- አቶ አለምአንተ አግደው


የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-51-63-84