Search

 የልዩ ልዩ ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት

አደረጃጀት

ዚህ ደይሬክቶሬቱ አራት ማስተባበሪያዎች የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-

በሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች ማስተባሪያ፣

በህገወጥ ድርጊት የሚፈጸሙ ወነጀሎች ማስተባበሪያ፣

የልዩ ልዩ ወንጀሎች ማስተባበሪያ እና

በወንጀል የተገኘ ንብርት ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባበሪያ ናቸው፡፡


በሥራ ክፍሉስርክትትልየሚደረግባቸውወንጀሎችምንነት /ባሕርይ/

በዚህ የሥራ ክፍል ስር ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮች በዋናነት በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ ላይ የተዘረዘሩት ወንጀሎችን የሚመለከት እና በተለያዩ አዋጆች የተደነገጉ የወንጀል ጥፋቶች ሲሆኑ ኢኮኖሚክ፣ ድንበር ዘለል እና የተደራጁ እንዲሁም ሀገራዊ ደህንነትን የሚነኩ ወንጀሎችን እና የሙስና ወንጀሎችን አይመለከትም፡፡ የወንጀሎቹ ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-


ወታደራዊ ወንጀሎች (ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 284-337) ሆኖ የፖሊስ አባላትን (አንቀጽ 340) በተመለከተ ብቻ የሚታይ ይሆናል፤


የታወቁ ማህተሞችን፣ ቴምብሮችን፣ ምልክቶች፣ ሚዛኖችንና መለኪያዎችን ወደ ሀሰት መለወጥ (ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 363-365 እና 368)፤


በህዝብ አመኔታ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 375-390) ይሁን እንጂ የንግድ ወይም ተላላፊ የዋስትና ሰነዶችን ወደ ሀሰት መለወጥና ማጥፋት (አንቀጽ 382) እና የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ወረቀቶችንና የማጓጓዣ ወረቀቶችን ወደ ሀሰት መለወጥና በእነዚሁ መገልገልን (አንቀጽ 384) አይመለከትም፤


የመንግሰት ሰራተኞች የስራግዴታን በአግባቡባ ለመወጣት የሚፈጸም ወንጀል (የወንጀል ህግ አንቀጽ 420-426)፤


ሌሎች ሰዎች በመንግስት ስራ ላይ የሚፈጽሟቸው ወንጀሎች (የወንጀል ህግ አንቀጽ 432-442)፤


በፍትህ አስተዳደር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ህግ አንቀጽ 443-465)፤


በህዝብ ደህንነት፣ ሰላምና ተረጋግቶ መኖር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ህግ አንቀጽ 477-481 እና489-493) ይሁን እንጂ ከሽብርተኛነት፣ በመነገድ አላማ ወይምበ አደገኝነታቸው ለሚታወቁ ሰዎች የጦር መሳሪያን ማዘዋወር እና በሀገር ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ሌሎች ወንጀሎችን አይመከትም፤


በጤና ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ህግ አንቀጽ 514-547) ከዚህ ጋር ተያይዞ የምግብና መድሀኒቶች ቁጥጥር አዋጅን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ያካትታል፤


በሰው ህይወት፣ አካልና ጤንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539-579)፤


በሰው ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 580-606)፤


በክብር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613-619) ከመገናኛ ብዙሀን እና መረጃ ነጻነት አዋጅ ጋር ተያይዞ የሚፈጸም በዓቃቤ ህግ ክስ ሊቀርብባቸው የሚገባ ወንጀሎችን ይመለከታል፤


በመልካም ፀባይ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620-661)፤


የደን ጥበቃ አዋጅን በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል (አዋጅ ቁጥር 542/1999)፤


የአካባቢ ጥበቃ አዋጅን በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል (አዋጅ ቁጥር 299/1995፣ 300/1995)፤


የተሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን መድን ሽፋንን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል፤


አዋጅ ቁጥር 384/1996ን በመተላለፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፤


የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001ን በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል፤


የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል (አዋጅ ቁጥር 654/2001)፤


የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅን በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል (አዋጅ ቁጥር 699/2002) እና በሌሎች አዋጆች የተመለከቱ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ይመለከታል፤


የልዩል› ልዩ ወንጀሎቹ ደረጃእናየሚታዩበትንስፍራ


ከላይ የተጠቀሱት ወንጀሎች በፈጻሚዎቻቸው ማንነት፣ በወንጀል አፈጻጸሙ ሁኔታ፣ በወቅታዊ አንገብጋቢነታቸው ደረጃ፣ በማስረጃ ረገድ በሚኖራቸው ውስብስብነት መሰረት በማድረግ ወንጀሎቹን በልዩ፣ ከባድ እና መደበኛ ደረጃ መለየት አስፈላጊ ይሆናል፡፡


በዚህም መሰረት ከላይ የተፈጸሙት ወንጀሎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጥታ የሚሾሙ፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚሾሙ አመራሮች እና በክልል ምክር ቤት የሚሾሙ አመራሮች በሚሆንበት ወቅት፤


ከዚህ በላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ በሥራ ክፍሉ አማካኝነት የሚታዩ ጉዳዮች፡-


ማስረጃ አሰባሰብ ውስብስብነታቸው እና የወንጀል ድርጊቱን በማስረጃ ለማረጋገጥ ከፍተኛ የሰው ሀይል፣ የባለሙያ ስብጥር እና የገንዘብ ሀብት የሚጠይቁ ጉዳዮች ለምሳሌ እንደ የሰው ግድያ ያሉ ወንጀሎች፤


ሁለት ክልሎችን ወይም በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት እና ከሁለት በላይ የከተማ አስተዳደር አካላት (ክፍለ ከተሞችን) የሚያነካካ የወንጀል ድርጊት በሚሆንበት ጊዜ፤


በክብር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በሚሆኑበት ጊዜ ተበዳዩ በሚኒስቴር ወይም በኮሚሽነር ደረጃ ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ከሆነ፤


የተፈጸመው ወንጀል ከወቅታዊነቱ ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የህዝብ ጥያቄ ያለበት እና መንግስትም በጥብቅ የሚከታተለው ጉዳይ ከሆነ፤


ከላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ ወንጀሎች ደረጃቸው ከባድ ይሆናል፡፡


ከላይ ከተገለጹት ውጪ ያሉት ወንጀሎች በደረጃቸው መደበኛ ሲሆኑ የሚታዩትም በመደበኛነት በጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በክ/ከተማ ደረጃ በሚቋቋሙት የታችኛው እርከን የስራ ክፍሎች አማካኝነት ይሆናል፡፡


በተዋረድ ያሉት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሥራ ክፍሎች ከላይኛው እርከን ወደ ታችኛው እርከን እንደ አስፈላጊነቱ ጉዳዮችን በውክልና መስጠት ይችላሉ፤


በስራ ክፍሉ  በማዕከል ደረጃ የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች

የስራ ሂደቱ በምድብ ጽ/ቤት የሚታዩ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮችን መከታተሉ እንደጠበቀ ሆኖ ራሱ በስራ ክፍሉ በማዕከል ደረጃ የሚያዙ ጉዳዮችን በመከታተል የሚሰራ ይሆናል፡፡ በስራ ክፍሉ የሚታዩ ጉዳዮች፡-

የግድያ ወንጀል፣

የትራፊክ ህግ በመጣስ የሚፈፀሙ የግዲያ ወንጀል፣

ከብዙ ሰዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ውስብስብ ወንጀሎች፣

አንድን ጥቅም ለማግኘት ወይም ገንዘብ ለማግኘት ተብሎ የሚፈፀሙ የሰዎች ጠለፋ ወንጀል፣

የከበሩ ማዕድናት ዝውውር ወንጀሎች፣

ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣

 

ዩ ልዩ ወንጀሎችን በተመለከተ በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ምድብ /ቤቶች ደረጃ ክትትል የሚደረግባቸው የወንጀል ጉዳዮች


ከዚህ በላይ በተመለከተው አግባብ ለዳይሬክቶሬቱ የተሰጠው የወንጀል ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በምድብ ጽ/ቤት ደረጃ የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩበትን አግባብ እና የወንጀሎቹን ጠቅላላ ዝርዝር ቀርቧል፡-


ዚህ መሰረት ልዩ ልዩ በሚል የተለዩት ወንጀሎች በምድብ ጽ/ቤቶች የሚታዩ የሚሆኑት፡-


በምርመራ ሂደታቸው ውስብስብ ያልሆኑ፣


በወቅታዊነታቸው በአንድ ማዕከል መያዛቸው አስፈላጊ የማይሆኑ እና


በግልጽ ለዳይሬክቶሬቱ ያልተሰጡ የወንጀል ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡


በጽ/ቤቶች ስልጣን ስር ከሚወድቁ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ህጋዊ ያልሆነ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀሎች በምድብ ጽ/ቤቶች የሚታዩ ይሆናሉ፡፡


በአጠቃላይ በማዕከል ደረጃ ከሚታዩት ከላይ በማዕከል እንዲታዩ ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉ ልዩ ልዩ ሌሎች ወንጀሎች በተቀመጠው መመዘኛና መርህ መሰረት በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጽ/ቤቶች ደረጃ የሚታዩ ይሆናል፡፡


በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ስር ስለሚደራጁ ማስተባበሪያዎች


በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ስር በተደራጁ ማስተባበሪያዎች የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች፡-


በሰዎች ላይ የሚፈፀሙ ከባድ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣ 


የግድያ ወንጀል፣

የትራፊክ  ህግ በመጣስ የሚፈፀሙ  የግዲያ ወንጀል፣

ከብዙ ሰዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ውስብስብ ወንጀሎች፣

አንድን ጥቅም ለማግኘት ወይም ገንዘብ ለማግኘት ተብሎ የሚፈፀሙ የሰዎች ጠለፋ ወንጀል፣

በሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈፀሙ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣

የከበሩ ማዕድናት ዝውውር ወንጀሎች፣

በከበሩ ማዕድናት የሚፈፀሙ የማታለል ወንጀል፣

በተደራጁ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጸሙ የከባድ ውንብድና ወንጀሎች

ቁጥራቸው በርከት ያለ ተጎጂዎች ያሉበት የአታላይነት ወንጀል

የልዩ ልዩ  ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣

ከዚህ በላይ በተደራጁት ማስተባበሪያዎች ስር እንዲታዩ ከተደረጉት የወንጀል ጉዳዮች ውጭ ያሉ በሥራ ክፍሉ  ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮች በዚህ ቡድን አማካኝነት የሚከናወኑ ይሆናሉ፡፡

እነዚህ ጉዳዮች በማስተባበሪያው በቀጥታ የሚታዩት ከ15 ዓመት በላይ የሚያስቀጡ በሚሆኑበት ጊዜ፣ ወንጀሎቹ በሁለት እና ከዚያ በላይ ክ/ከተሞች ሲፈፀሙ ወይም ደግሞ  በተለያየ ምክንያት ወንጀሉ በህብረተሰቡ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ከፍተኛ ሲሆን እንዲሁም ተከሳሹ የነበረው/የያዘው የሥልጣን ደረጃ ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ በሥራ ክፍሉ አማካኝነት ጉዳዩ መያዝ  ስለሚኖርበት በቡድኑ ክትትል የሚደረግበት ይሆናል፡፡ከዚህ በላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ የማይወድቅ ከሆነ ግን በክ/ከተማ ደረጃ በተደራጁት ጉዳዮቹ ክትትል የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

በወንጀል የተገኙ ንብረቶች ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ቡድን

ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች ለወንጀሉ መፈተሚያ የዋሉ ንብረቶችን ወይም ከወንጀሉ ፍሬ ሆነው የተገኙ ንብሬችን በመከታተከል እና በመለየት በህጉ መሰረት እንዲከበር እንዲወረስ እና በወንጀሉ ምክንያት የጠፋ ሃብት ወይም የደረሰ ጉዳት ካለ እንዲካስ የማድረግ ሃላፊነትን የሚወጣ ቡድን ይሆናል፡፡


 የኃላፊ ስም፡-  ወ/ሮ ወሰንየለሽ አድማሱ


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-33-38