Search

የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ይህ የስራ ሂደት በተቋሙ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራትና ለሕዝብ እና ለሚመለከተው አካላት እንዲደርስ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ኣና ከአጠቃላይ ሕብረተሰብ ጋር የሚደረጉ የሕዝብ ግንኙት ስራዎችን የሚመራ ሲሆን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነቶች፡-

 

የተቋሙ የበላይ ኃላፊ የቃል አቀባይነት ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው የቃል አቀባይነት ሥራን ይሰራል፣

 

የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተቋሙ ስትራቴጅያዊና ዓመታዊ የኮሙኒኬሽ ዕቅድ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ስትራቴዷና ዕቅድ ጋር አጣጥሞ ማዘጋጀት ፣ ለተቋሙ ሥራ አመራር አቅርቦ ማፀደቅ፣ ለመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማሳወቅና ተግባራዊ ማድረግ፣

 

በተቋሙ አስፈላጊውን ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ያለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ እንዲፈጠር፣ እንዲስፋፋና እንዲዳብር የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዲሠጡ ማቀድ፣ በሚመለከተው አካል ሊፈቀድም ተግባር ላይ ማዋል፣

 

ከመሥሪያ ቤቱ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ ፣ ፕሮግራም፣ ዕቅዶችና አፈፃፀሞች ጋር ተያያዥነት ያለቸው መልዕክቶች በመቅረጽ ለተቋሙ የሥራ አመራር አቅርቦ በማጽደቅ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማስራጨት ፣ግብረ-መልስ ማሰባሰብ፣

 

መሥሪያ ቤቱን በተመለከቱና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚዲያ ዘገባ ክትትል በማድረግ ትንተና በማዘጋጀት፣ ለበላይ ኃላፊ በማቅረብ የኮሙኒኬሽን ሥራን ማማከር፣

 

የመሥሪያ ቤቱ መረጃዎች በአግባቡ የሚሰባሰቡበትንና የሚደራጁበትን ሥርዓት መዘርጋትና ለሚዲያና ለማንኛውም አካል የመረጃ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ወይም አግባብ ካላቸው የተቋሙ አካላት ምላሽ እንዲሰጥበት ማድረግ፣

 

በተለያዩ ጊዜያት ከመንግስት የሚወጡ ወቅታዊ መልዕክቶችን ተቀብሎ ለህዝብ ግንኙነት ሥራው ጥቅም ላይ ማዋል፣

 

በሕብረተሰቡ፣ በባለድርሻ  አካላትና በተቋሙ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲቻል የተለያዩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ፣

 

በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መካከል ያለው ግንኙነት ውጤታማ ለማድረግ በመስራት ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ፣

 

በመሥሪያ ቤቱ የሥራ ሂደቶች መካከል ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት መዘርጋት ፣ ማስተባበር፣ ማስፈፀም፣

 

በመሥሪያ ቤቱ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች እንዲሁም ለብሔራዊ መግባባትና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ግልጽነትን ለመፍጠር የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀትና ማስተባበር፣

 

የመሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች  የመሥሪያ ቤቱን የልማት እንቅስቃሴዎች፣ አፈጻጸሞችንና ክንውኖችን እንዲጎበኙ ማቀድ ማስተባበርና ማስፈፀም፣

 

ለብሔራዊ መግባባትና ገጽታ ግንባታ የሚረዱ ነባርና አዳዲስ ዋና ዋና ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁነቶች ላይ እንዲሁም የፈጠራ ሁነቶችን ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ጋር በመመካከር ማቀድ፣ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፣

 

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደአስፈላጊነቱ የመሥሪያ ቤቱን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች ፣ ዕቅዶች፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ለመስተዋወቅ የሚያስችሉ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም ዝግጅቶችን ያቅዳል፣ ያደራጃል ያስፈጽማል፣

 

በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ የሚጫኑ መረጃዎች ይዘት የመንግሥትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የተቋሙን ተልዕኮ ያገናዘበ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ድረ-ገጽ ጋር በተመጋገበ መልኩ እንዲጫን  ያደርጋል፣

 

የመሥሪያ ቤቱን መረጃዎች በፎቶግራፍ፣ በኦዲዮና ቪዲዮ ቀረጻና ሕትመት በሥራ ክፍሉ እና በተባባሪዎች አማካኝነት ማዘጋጀትና ጥቅም ላይ ማዋል፣

 

ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በየጊዜው መረጃዎችን አደራጅቶ መስጠትና እንደ አስፈላጊነቱ የሥራ ትብብር ማድረግ፣

 

የውጭ ሀገር ጋዜጠኞችና ፊልም አንሺዎች ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ ፈቃድ ይዘው ሲመጡ ሥራቸውን ለማቀላጠፍ አስፈላጊውን ህጋዊ የሥራ ትብብር ማድረግ፣

 

መሥሪያ ቤቱን የሚመለከቱ የማስታወቂያ ሥራዎች በመንግሥት በሚወጡ የማስታወቂያና የስፖንሰርሺፕ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ፣ ለሕዝብ ግልጽና ትክክለኛ የሆነ መልዕክት ይዘው መውጣታቸውንና ሥርጭታቸውም የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004ን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ፣

 

የመሥሪያ ቤቱን መረጃ የሚሰጡ ወኪሎች ወይም ቅርንጫፎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚኖሩበት ሁኔታን ማመቻቸት፣

 

በመሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ ጥናት ማካሄድ፣ አስተያየት ማሰባሰብ፣ መገምገም፣ አሰራሩ የሚሻሻልበትን አቅጣጫ መቀየስና ጥናቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

 

በሀገር አቀፍና በተቋም ደረጃ ያልተጠበቀ ክስተቶች /ቀውስ/ ሊፈጠር ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ ክስተቶች ቀውሶች/ በመገንዘብ ማቀድና ተግባራዊ ማድረግ፣ ከሌሎች አካላት ጋር በመመካከር መረጃ ማሰራጨትና የማረጋጋት ተግባር ማከናወን፣

 

የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሶስት ወር፣ በስድስት ወር በዘጠኝ ወርና በዓመት ወቅቱን ጠብቆ ለበላይ አካልና ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ማቅረብ፣ በተጨማሪም በተደራጀው የፌዴራል የህዝብ ግንኙነት ክላስተር ላይ ሪፖርቱን አቅርቦ በማስገምገም የሚሰጠውን ግብረ-መልስ ተግባራዊ ማድረግ ናቸው፡፡


የኃላፊ ስም፡- አቶ ዝናቡ ቱኑ

የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-15-65-30